Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ አሜሪካና በካሪቢያን በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ አሜሪካና በካሪቢያን በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ ማለፉ ተነገረ።

ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በብራዚል መመዝገቡን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም በሜክሲኮ ከ23 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው።

በሁለቱ ሃገራት ከቫይረሱ ጋር ተያይዞ ምንም አይነት የእንቅሳቀሴ ክልከላም ሆነ ገደብ አልተጣለም።

ይህም ለቫይረሱ መዛመት አይነተኛ ሚና እንዳለው ባለሙያዎች ገልጸዋል።

ደቡብ አሜሪካ አሁን ላይ ከየትኛውም አካባቢ በበለጠ የቫይረሱ መገኛ ሆኗል ነው የተባለው።

ቫይረሱ ከፍ ያለ ጉዳት ያስከትል እንጅ አሁንም በከፍተኛ ደረጃ ተዛምቷል የሚባልበት ደረጃ ላይ አለመድረሱን ባለሙያዎች እየገለጹ ነው።

ይህ ደግሞ ቀጣዮቹን ሳምንታት ከባድ ያደርገዋል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.