Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሉሲዎቹ ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የአንደኛ ዙር ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታውን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከብሩንዲ ጋር አድርጓል፡፡ ሉሲዎቹ በመደበኛ የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በመለያ ምት 5 ለ 3 ተሸንፈዋል፡፡ በዚህም ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጪ ሲሆኑ ቡሩንዲ ወደ ቀጣይ ዙር አልፋለች።
Read More...

የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ከክለቦች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባው ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የእግር ኳሱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ከክለቦች ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳስቧል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አመራሮችና ስራ አስፈፃሚ አባላት ጋር በእግር ኳሱ ዕድገት…

በአዲስ አበባ ዋንጫ ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ለፍጻሜ ደረሱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ዋንጫ ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሰዋል፡፡ በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ከኢትዮጵያ መድን ጋር የተጫወተው ሃድያ ሆሳዕና በመለያ ምት 5 ለ 4 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለዋንጫ ጨዋታ ማለፉን አረጋግጧል። በተመሳሳይ ቅዱስ ጊዮርጊስን የገጠመው ኢትዮጵያ ቡና በመለያ ምት 5 ለ…

የሰሜን ለንደን ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ከቶተንሃም ሆትስፐር ያደርጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡ ቶተንሃም የጨዋታ ብልጫ በወሰደብት የሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ክርስቲያን ሮሜሮ በራሱ ላይ ባስቆጠራት ግብ መምራት ቢችልም ሰን ሁንግ ሚን ቶተንሃምን አቻ አድርጎ የመጀመሪያውን አጋማሽ አንድ አቻ አጠናቅቀዋል፡፡…

አትሌት ትዕግስት አሰፋ የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን ሰበረች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች፡፡ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ በመግባት ነው ክብረወሰኑን የሰበረችው። ኬኒያዊቷ አትሌት ብሪግድ ኮስጌይ በፈረንጆቹ 2019 በ2 ሰዓት ከ14 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ በመግባት ይዛው…

ማንቼስተር ሲቲ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ተጋጣሚውን ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ሲቲ÷ ፊል ፎደን እና ኤርሊንግ ሃላንድ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ነው ተጋጣሚውን የረታው፡፡ ሮድሪ በ46ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡ በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር ክርስታል ፓላስ…

ሉሲዎቹ ከቡሩንዲ አቻቸው ጋር ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታው 9 ሰዓት ከብሩንዲ አቻው ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አካሂደዋል ። በዚህም ሉሲዎቹ በመጀመሪያው አጋማሽ በረድኤት አስረሳኸኝ ጎል ተጋጣሚያቸውን 1 ለ 0 መምራት ችለው ነበር፡፡ ሆኖም በሁለተኛው አጋማሽ የብሩንዲ ሴቶች ብሄራዊ…