Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የክርስቲያኖ ሮናልዶ ልጅ ለአልናስር ከ13 ዓመት በታች ቡድን ፈረመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የክርስቲያኖ ርናልዶ ልጅ ሮናልዶ ጁኒየር ለአልናስር ከ13 ዓመት በታች መፈረሙ ተሰምቷል፡፡ ሮናልዶ ጁኒየር በቀጣይ ቀናት በአልናስር አካዳሚ ልምምድ ማድረግ ይጀምራል የተባለ ሲሆን ፥ 7 ቁጥር መለያ እንደሚሰጠውም ነው የተገለፀው፡፡ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የእግርኳስ ክህሎቱን ሲያሳይ የነበረው ሮናልዶ ጁኒየር ከአባቴ ጋር የመጫዎት ፍላጎት አለኝ ማለቱ አነጋጋሪ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦…
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ3ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድንን የገጠመው ወላይታ ድቻ በአብነት ደምሴ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡ በተመሳሳይ 12 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና እና ፋሲል ከነማ ባዳረጉት ጨዋታ ጊት ጋት ጉት በራሱ…

ኔማር  ባጋጠመው ጉዳት ከ8 እስከ 10 ወራት ከጨዋታ ሊርቅ ይችላል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው ኮከብ ኔማር ጁኒየር ባጋጠመው የመገጣጠሚያ ጉዳት ከ8 እስከ 10 ወራት ከጨዋታ ሊርቅ እንደሚችል ተገልጿል፡፡ የተጨዋቹ ጉዳት 90 ሚሊየን ዩሮ ፈሰስ በማድረግ ተጨዋቹን ከፒ ኤስ ጂ ላስፈረመው የሳውዲው ክለብ አል ሂላል መጥፎ ዜና ነው ተብሏል፡፡ የ31 ዓመቱ አጥቂ በአለም ዋንጫ ማጣሪያው ብራዚል ከኡራጓይ…

ፔር ሉዊጂ ኮሊና – የዓለማችን ምርጡ የእግር ኳስ ዳኛ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፈረንጆቹ 1998 እስከ 2003 ለሥድስት ተከታታይ ዓመታት “የዓለማችን ምርጡ ዳኛ” የሚል ማዕረግ ሰጥቶታል፡፡ በፈረንጆቹ የካቲት 13 ቀን 1960 በጣሊያን ቦሎኛ የተወለደው ፔር ሉዊጂ ኮሊና የዳኝነት ሕይወቱን በ18 ዓመቱ የጣሊያን ሴሪ ሲ 1 ጨዋታ በመዳኘት “ሀ” ብሎ ጀመረ፡፡…

በቶሮንቶ ዋተርፍሮንት ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በካናዳው የቶሮንቶ ዋተርፍሮንት ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል። በሴቶች ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ከ1 እስከ 4 ተከታትለው በመግባት አሸናፊ ሆነዋል። ውድድሩን አትሌት ቡዜ ድሪባ 2 ሰአት ከ23 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ስትሆን ዋጋነሽ መካሻ በ1 ሰከንድ ልዩነት ሁለተኛ…

የኢትዮጵያ የሴቶች ከ20 አመት በታች ቡድን ኢኳቶሪያል ጊኒን 4 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ድል ቀንቷታል። ከኢኳቶሪያል ጊኒ የተጫወተው የሴቶች ወጣት ቡድን ጨዋታውን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በመጀመሪያው ጨዋታ አንድ አቻ የተለያዩ ሲሆን፥ የዛሬውን ውጤት ተከትሎ በድምር ውጤት የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20…

በፕሪሚየር ሊጉ ባህር ዳር ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 4 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ሳምንት መርሐ ግብር  ባህር ዳር ከተማ መቻልን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ ዛሬ 9 ሰዓት ባህር ዳር ከተማ እና መቻል  ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን÷ ባህር ዳር ከተማ  2ለ 1 አሸንፏል፡፡ የባህር ዳር ከተማን የማሸነፊያ ጎሎች  ፍሬው…