Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ጋና ገባ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የሚሳተፈው ከ90 በላይ ሰዎችን ያካተተው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት ጋና አክራ ገብተዋል። ልዑኩ ከአጭር እስከ መካከለኛ ርቀት የሚወዳደሩ አትሌቶች እና የሴቶች የቅርጫት ኳስ ቡድንን ያካተተ ነው፡፡ በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱም በጋና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ ፍቅሬ ጎሳዬን ጨምሮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ተገኝተዋል። አምባሳደሩም ለልዑካን ቡድኑ አባላት የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልዕክት…
Read More...

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሻሸመኔ ከተማን 2 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሻሸመኔ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች አማኑኤል ኤርቦ በ70ኛው እና 86ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በበላይነት መምራት ጀምሯል።…

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻልና ሐዋሳ ከተማ ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 18ኛ ሳምንት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻልና ሐዋሳ ከተማ ድል ቀናቸው። ምሽት 1:00 ላይ በተካሄደው የመቻል እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ መቻል ጨዋታው እንደተጀመረ ምንይሉ ወንድሙ በሶስተኛው እና አቤል ነጋሽ በስድስተኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች መቻል 2 ለ 0 አሸንፏል።…

በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሜዳሊያዋን አገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሜዳሊያዋን አግኝታለች፡፡ ዛሬ በተደረገው ከ23 አመት በታች የነጠላ ወንዶች ብስክሌት ውድድር ኪያ ጀማል 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አግኝቷል። ደቡብ አፍሪካ ውድድሩን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ ሞሪሺየስ 3ኛ ደረጃን ይዛ ጨርሳለች። በብስክሌት…

የዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2023/24 የዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡ በድልድሉ መሠረትም ኤሲ ሚላን ከሮማ የሚፋለሙ ይሆናል፡፡ እንዲሁም ሊቨርፑል ከአታላንታ÷ ባየርሊቨርኩሰን ከዌስትሃም ዩናይትድ  ጋር ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ቤኔፊካ ከማርሴ ጋር መደልደላቸውን የወጣው መርሐ-ግብር ያመላክታል፡፡

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡ በዚሁ መሠረትም አርሰናል ከባየርን ሙኒክ ጋር የሚገናኙ ይሆናል፡፡ እንዲሁም አትሌቲኮ ማድሪድ ከቦርሲያ ዶርትመንድ፤ ሪያል ማድሪድ ደግሞ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ተድልድለዋል፡፡ በተጨማሪም ፓሪሴንት ዠርሜይን ከባርሴሎና ጋር በሩብ ፍፃሜው የሚገናኙ ይሆናል፡፡…

በግራንድ አፍሪካን ራን ለሚሳተፉ አትሌቶች የመኪና ሽልማት ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ዋሽንገተን ዲሲ በሚካሄደው የግራንድ አፍሪካ ራን ለሚሳተፉ አትሌቶች የመኪና ሽልማት መዘጋጀቱ ተገለፀ፡፡ ግራንድ አፍሪካን ራን በየአመቱ ጥቅምት በገባ በሁለተኛዉ ቅዳሜ በዋሺንግተን ዲሲ ከተማ የሚደረግ የ5 ኪሎሜትር የሩጫ ዉድድር ነዉ። በዚህ ውድድር ለሚሳተፉ በአሜሪካ ግዙፉ የቶዮታ መኪና አከፋፋይ የሆነው…