Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የአራተኛ ሳምንት የዛሬ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 16 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል። 9 ሰአት ላይ በተደረገ ጨዋታ ሀምበርቾ ከሀድያ ሆሳዕና ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። ምሽት 12 ሰአት ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ የአምናው ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከተማ ተገናኝተዋል። ጨዋታውን አዳማ ከተማ 2 ለ 0 መምራት ቢችልም ከዕረፍት መልስ በተቆጠሩበት ሁለት ጎሎች በአቻ ውጤት አጠናቋል። ሀይደር ሸረፋ በፍጹም ቅጣት ምት እንዲሁም ዊልያም ሰለሞን በጨዋታ ለአዳማ…
Read More...

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጣና ሞገዶቹ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአራተኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባሕርዳር ከተማ ወልቂጤ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡ 12፡00 ላይ በአዳማ ሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተደረገው ጨዋታ÷ ሀብታሙ ታደሰ የባሕርዳር ከተማን ሦስት ጎሎች በማስቆጠር ሃትሪክ ሠርቷል፡፡ ሃትሪኩም እስካሁን ባለው የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ውድድር…

ሳንድሮ ቶናሊ ለ10 ወራት ከእግርኳስ ታገደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኒውካስል ዩናይትዱ የመሀል ክፍል ተጫዋች ሳንድሮ ቶናሊ ከስፖርት ውርርድ ጋር በተያያዘ ለ10 ወራት ከእግርኳስ መታገዱን የጣሊያን እግኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ ወጣቱ ጣሊያናዊ ኤሲ ሚላን በነበረበት ወቅት ህገ ወጥ የእግርኳስ ደህረ ገፆችን በመጠቀም የእግር ኳስ ውርርድ ማድረጉ በመረጋገጡ ነው ውሳኔው የተላለፈበት፡፡…

ሉሲዎቹ ከናይጀሪያ አቻቸው ጋር 1 ለ 1 ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሎምፒክ ማጣሪያ ጨዋታ ከናይጄሪያ አቻው ጋር ጨዋታውን ያከናወነው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያየ። ሁለተኛው ዙር የመጀመርያ ጨዋታ ዛሬ ቀን 9:30 በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተካሄደ ሲሆን ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል። የመልሱ ጨዋታ ጥቅምት 20 አቡጃ ላይ እንደሚካሄድ ከኢትዮጵያ…

ሲዳማ ቡና ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክቷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ4ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ሻሸመኔ ከተማን የገጠመው ሲዳማ ቡና 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡ የሲዳማ ቡናን የድል ጎሎች ደስታ ዮሐንስ ፣ ደግፌ አለሙ እና አበባየሁ ዮሐንስ ሲያስቆጥሩ÷ የሻሸመኔ ከተማን ብቸኛ ጎል እዬብ ገ/ማርያም አስቆጥሯል፡፡ ውጤቱን ተክትሎ ሲዳማ ቡና ከተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ…

ሉሲዎቹ የናይጀሪያ አቻቸውን ዛሬ ያስተናግዳሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሎምፒክ ማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከናይጀሪያ አቻው ጋር በዛሬው እለት ጨዋታውን ያከናውናል፡፡ ሁለተኛው ዙር የመጀመርያ ጨዋታ ቀን 9:30 በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚካሄድ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ሉሲዎቹ ለማጣሪያ ጨዋታው ላለፉት ስድስት ቀናት አካላዊ እና…

ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና የገንዘብ ቅጣት ተላለፈባቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና በፈፀሟቸው የዲሲፕሊን ጥሰቶች የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ሥነ-ስርዓት ኮሚቴ በ3ኛ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ላይ ከዳኞች እና ታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በክለብ ደረጃ ሲዳማ ቡና ከፋሲል…