Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

መቻል እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ20ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለግብ አቻ ተለያዩ፡፡ መቻል በ40 ነጥብ ፕሪሚየር ሊጉን እየመራ ሲሆን÷ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ38 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለተኛ ላይ ይገኛል፡፡ እንዲሁም ምሽት 1 ሠዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ÷ ባህርዳር ከተማ በቸርነት ጉግሳ ብቸኛ ጎል ሻሸመኔ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
Read More...

ማንቼስተር ሲቲ ክሪስታል ፓላስን 4 ለ 2 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ32ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ማንቼስተር ሲቲ ክሪስታል ፓላስን 4 ለ 2 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡ ሲቲ ከመመራት ተነስቶ ነው ተጋጣሚውን የረታው፡፡ የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኬቨን ዴብሮይን (2)፣ ኤርሊንግ ሃላንድ እና ሪኮ ሌዊስ ከመረብ ሲያሳርፉ÷ የክሪስታል ፓላስን ጎሎች ደግሞ…

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማና ኢትዮጵያ ቡና አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 20ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና አሸነፉ። 12፡00 ላይ በተካሄደው የድሬዳዋ ከተማ እና ፋሲል ከነማ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ለድሬዳዋ ከተማ በ73ኛው ደቂቃ ካርሎስ ዳምጠው፤ በ76ኛው ደቂቃ እስማኤል አብዱል ጋንዩ…

ደቡብ አፍሪካዊው እግር ኳስ ተጫዋች የመኪና ስርቆት በሚፈጽሙ ወንጀለኞች መገደሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካ እና የካይዘር ችፍስ ተከላካይ መስመር እግር ኳስ ተጫዋች የሆነው ሉክ ፍሉርስ በጆሃንስበርግ ከተማ የመኪና ስርቆት በሚፈጽሙ ወንጀለኞች በጥይት ተመትቶ ህይወቱ ማለፉ ተገለጸ። ክለቡ እንዳስታወቀው÷ የ24 ዓመቱ ተከላካይ በጆሃንስበርግ ከተማ ሆንዲው በተባለው ሰፈር መኪኒናውን ነዳጅ ለመሙላት እየተጠባበቀ…

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በክለቦች ብቻ የሰራው ሀትሪክ 55 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአልናስሩ የፊት መስመር ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በክለቦች ውስጥ ባለው የእግርኳስ ሕይወት በአንድ ጨዋታ ላይ ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር (ሃትሪክ) ያለውን ታሪክ 55 አድርሷል። ትናንት ምሽት በሳኡዲ ፕሮ ሊግ አል ናስር አብሃን 8 ለ 0 በሆነ ውጤት ባሸነፈበት ጨዋታ ሮናልዶ ከእረፍት በፊት ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር ሃትሪክ…

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የተበረከተላትን የኒሻን ሽልማት ተረከበች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የተበረከተላትን የወርቅ ጨረር ያለው የኒሻን ሽልማት ተረክባለች። ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በስፖርት ዲፕሎማሲ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ቀደም ሲል ከጃፓን መንግስት የክብር ኒሻን ሽልማት የተበረከተላት መሆኑ ይታወሳል፡፡ በጃፓን እና…

ለ45ኛው የዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ልዑክ የእውቅና መርሐግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰርቢያ ቤልግሬድ በተካሄደው 45ኛ የዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳትፎ በድል ለተመለሰው የልዑካን ቡድን የእውቅናና የማበረታቻ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡ በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ÷የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑን በመግለፅ ለቀጣይ ውድድሮች ትኩረት…