Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 1ኛ ዙር የውድድር መርሐ- ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2016 የውድድር ዓመት አንደኛ ዙር የውድድር መርሐ- ግብር ይፋ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ሕዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጅማ አባጅፋር እና ወልዲያ ከተማ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ እንደሚጀመር ከወጣው መርሐ- ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ አዳማ ከተማ እና መቻል ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 5ኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል። 9 ሰአት ላይ በተካሄደ የመጀመሪያው ጨዋታ አዳማ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የአዳማ ከተማን ግቦች አብዲሳ ጀማል እና አሰጋኸኝ ጴጥሮስ (በራሱ ላይ) ሲያስቆጥሩ ዘርዓይ ገብረስላሴ ደግሞ የድሬዳዋ ከተማን ብቸኛ…

ሉሲዎች የመልስ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2024 ኦሎምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከናይጀሪያ አቻው ጋር ይካሄዳል። ጨዋታው ምሽት 12፡10 ላይ በአቡጃ አቢዮላ ስታዲየም የሚደርግ መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ሉሲዎቹ የመልስ ጨዋታቸውን ለማድረግ ከቀናት በፊት…

ሊዮኔል ሜሲ ለ8ኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊዮኔል አንደሬስ ሜሲ የ2023 ባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ ሆኗል፡፡ የ2022/ 2023 የባላንዶር አሸናፊ ሽልማት ሥነ- ሥርዓት በዛሬው ዕለት በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ተካሂዷል፡፡ በዚህም በወንዶች አርጀንቲናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ የዓለማችን ምርጥ ተጫዋች በመባል ለ8ኛ ጊዜ የባሎንዶር ሽልማትን ተቀዳጅቷል፡፡…

በአሜሪካ በተካሄደ ኢንተርናሽናል ማርሻል አርት ውድድር ኢትዮጵያ 3ኛ ደረጃን ያዘች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኦርላንድ ፍሎሪዳ ከተማ በተካሄደው ኢንተርናሽናል ማርሻል አርት ፌስቲቫል እና ውድድር ኢትዮጵያ በኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች፡፡ ሦስት ወርቅ እና አንድ የነሐስ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ነው ኢትዮጵያ በኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ውድድር ከአሜሪካ እና ስኮትላንድ በመቀጠል ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ…

የቀድሞው የስፔን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዚዳንት የሶስት አመት ዕግድ ተላለፈባቸው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በቀድሞው የስፔን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዚዳንት ሉዊስ ሩቢያሌስ ላይ ዕገዳ አስተላለፈ። ፊፋ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከማንኛውም ስፖርታዊ ጉዳዮች ለሶስት አመታት እንዲታገዱ ነው ውሳኔ ያሳለፈው። ሩቢያሌስ ስፔን አሸናፊ በሆነችበት የሴቶች የዓለም ዋንጫ የሽልማት ሥነ…

አትሌት ደሬሳ ገለታ በቤጂንግ ማራቶን ውድድር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ደሬሳ ገለታ እና አትሌት ይሁንልኝ አዳነ በቤጂንግ 2023 ማራቶን ውደድር አሸንፈዋል፡፡ አትሌት ደሬሳ ገለታ ርቀቱን 2 ሰዓት 7 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ መሆን ችሏል፡፡ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ይሁንልኝ አዳነ ደግሞ ርቀቱን 2 ሰዓት 7 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመጨረስ…