Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ቶተንሃም ድል ሲቀናው ኒውካስትል በሉተን ተሸንፏል

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 13 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት መርሓ ግብር ማምሻውን አራት ጨዋታዎች ተደርገዋል። 12 ሰአት ላይ በተካሄዱ ጨዋታዎች በርንሌይ እና ሉተን ታዎን ያልተጠበቀ ውጤት አስመዝግበዋል። ወደ ክራቨን ኮቴጅ በማምራት ከፉልሃም ጋር የተጫወተው በርንሌይ ጨዋታውን 2 ለ 0 አሸንፏል። ኦዶበርት እና በርግ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል። በሜዳው ኒውካስትል ዩናይትድን ያስተናገደው ሉተን ታዎን ደግሞ በአንዲ ቶውሴንድ ጎል የ1 ለ 0 ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል። አሰልጣኝ…
Read More...

ማንቼስተር ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊጉ 8ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዘንድሮው ውድድር ዓመት ስምንተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡ በለንደን ስታዲየም ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር የተጫወተው ማንቼስተር ዩናይትድ ጃሬድ ቦዌን እና ሞሃመድ ኩዱስ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡ የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ቡድን…

ቪክቶር ኦሲሜን በናፖሊ ኮንትራቱን አራዘመ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ናይጀሪያዊው አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜን በናፖሊ እስከ 2026 የሚያቆየውን ተጨማሪ ኮንትራት ውል ፈርሟል፡፡ በአዲሱ ኮንትራት ሥምምነት የወጣቱ አጥቂ ፈላጊ የሆነ ክለብ 130 ሚሊየን ዩሮ መክፈል ይጠበቅበታል። ኦስሜን በ2022 የስኮዲቶ ሻምፒዮን ከሆነው ናፖሊ ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ የቻለ ሲሆን 26 ጎሎችን…

የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ከክለቡ ጋር ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰርቢያዊው የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣን ኒኮላ ካቫዞቪች ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል፡፡ የክለቡ የአካል ብቃት አሰልጣኙ ማርኮ ቭላስቪችም ባስገቡት መልቀቂያ መሰረት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር መለያየታቸውን ክለቡ በሳምንታዊ የሬዲዮ ፕሮግራሙ ላይ አስታውቋል፡፡ ሁለቱ አሰልጣኞች ያለፉትን አምስት ወራት ቡድኑን ለቅድመ ውድድር…

ፊፋ የ2 ነጥብ 79 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የእግርኳስ ማህበር (ፊፋ) ለአባል ሀገራቱ እግር ኳስ ልማት የሚውል የ2 ነጥብ 79 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገ፡፡   በድጋፉ በስድስቱ የአሀጉራት ኮንፌዴሬሽን ውስጥ የሚገኙ 1 ሺህ 600 በላይ ፕሮጀክቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡   የፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያን ኢንፋቲኖ÷ ከእግር…

ሊዊስ ሱዋሬዝ ኢንተር ሚያሚን ለመቀላቀል ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኡራጓዊው አጥቂ ሉዊስ ሱዋሬዝ በጥር የዝውውር መስኮት የአሜሪካውን ክለብ ኢንተር ሚያሚን ለመቀላቀል መስማማቱ ተገለፀ፡፡ ሱዋሬዝ በአንድ ዓመት የኮንትራት ውል ወደ ሜጀር ሊግ ሶከር ለማምራት በቃል ደረጃ ሥምምነት ላይ መድረሱ የተገለፀ ሲሆን÷ ይፋዊ ፊርማው በቅርቡ ይገለፃል ተብሏል፡፡ ሥምምነቱን ተከትሎም ሱዋሬዝ…

የሩሲያ እግርኳስ ወደ ኤሲያ ኮንፌዴሬሽን መዛወር እንደማይፈልግ ባለስልጣናቱ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ብሄራዊ ቡድን እና ክለቦች ወደ ኤሲያ ኮንፌዴሬሽን እንዲዛወሩ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ የሞስኮ እግርኳስ ባለስልጣናት ውድቅ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡ የሩሲያ ብሄራዊ ቡድን እና ክለቦች በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት በፊፋ እና ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድሮች አንዳይሳተፉ ማዕቀብ ተጥሎባቸው መቆየቱ…