Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የኢትዮጵያ የአጭር፣ መካከለኛ፣ የእርምጃና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ውድድር መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የአጭር፣ መካከለኛ፣ የ3000 ሜትር መሰናክል፣ የእርምጃ እና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ውድድር እየተካሄደ ነው። አትሌቲክስ ውድድሩ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ስታዲየም መካሄድ መጀመሩን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባወጣው መረጃ አስታውቋል። በዛሬው እለትም የአሎሎ ውርወራ ማጣሪያና ፍፃሜ፣ የስሉስ ዝላይ ማጣሪያና ፍፃሜ ውድድሮች እንደሚካሄዱ የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል። እንዲሁም ከ100 ሜትር እስከ 800 ሜትር የማጣሪያ ውድድሮች እንደሚካሄዱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን…
Read More...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 6፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ስታዲየም በነገው ዕለት ይጀመራል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአጭር፣ በመካከለኛ ርቀት፣ በ3 ሺህ ሜ.መሰናክል፣ በእርምጃና በሜዳ ተግባራት ከታህሳስ 7 እስከ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበበ ስታዲየም ነው የሚካሄደው፡፡ በመክፈቻው እለትም የአሎሎ ውርወራ…

በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፍነው ቅዳሜና እሁድ በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል። በቻይና በተካሄደ የሼንዚን የወንዶች ማራቶን ውድድር ታደሰ ቶላ እና ተረፈ ደበላ ተክታትለው በመግባት ከአንድ እስከ ሁለተኛ ያለውን ደረጃ ሲይዙ በቀለ ሙሉነህ ሰባተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።…

የአትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያና 14ኛው የካሳማ የግማሽ ማራቶን ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያና 14ኛው የካሳማ ከተማ የግማሽ ማራቶን ውድድር ተካሄደ። በውድድሩ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸንፈዋል። በግማሽ ማራቶን ውድድሩ በወንዶች አትሌት አብዮት አብነት እንዲሁም በሴቶች ደግሞ አትሌት እታለማሁ ስንታየሁ አሸናፊዎች ሆነዋል። ውድድሩን አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣…

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨታዎች በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል። ስሁል ሽረ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መቐለ ላይ በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ባካሄዱት ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ባህር ዳር ከነማን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ 1 ለ 0 በሆነ…

ሰበታ ከተማ ለአራት ዓመታት የሚቆይ የ18 ሚሊየን ብር የስፓንሰርሽፕ ስምምነት ከሜታ አቦ ቢራ ጋር ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው ዓመት ከረጅም ጊዜ በኋላ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን የተቀላቀለው ሰበታ ከተማ ለአራት ዓመታት የሚቆይ የ18 ሚሊየን ብር የስፓንሰርሽፕ ስምምነት ከሜታ አቦ ቢራ ጋር ተፈራረመ፡፡ የስፓንሰርሽፕ ስምምነቱ በትናትናው ዕለት የክለቡ የበላይ ጠባቂ እና የሰበታ ከተማ ከንቲባ አቶ ብርሃኑ በቀለ እና የክለቡ…

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሲጠቀምበት የነበረውን አርማ አሻሻለ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለረዥም አመታት ሲጠቀምበት የነበረውን አርማ አሻሻለ። ትናንት 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው ፌዴሬሽኑ በጉባኤው ፌዴሬሽኑን አይገልጽም እንዲሁም አላስፈላጊ ምልክቶች ተካተውበታል በሚል ቅሬታ ሲቀርብበት የቆየውን አርማ አሻሽሏል። በዚህም በአርማው መካከል የነበረው…