Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 15 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ተከታትለው በመግባት አሸናፊ ሆነዋል። በወንዶች አትሌት ኦሊቃ አዱኛ 2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል። ኬንያዊው አትሌት ኤሪክ ኪፕሮኖ 2ኛ ደረጃን ሲይዝ ከ3ኛ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል። በዚህም መሰረት ፀዳት አበጀ 3ኛ፣ ሌንጮ ተስፋዬ 4ኛ፣ ይታያል አጥናፉ 5ኛ፣ ይሁንልኝ አዳነ 6ኛ፣ አይቼው በንቲ 7ኛ፣ ሰይፉ…
Read More...

አሰልጣኝ ሁሴን ሺቦ የአመቱ የአፍሪካ ምርጥ አትሌቲክስ አሰልጣኝ ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን በ2019 በአትሌቲክሱ ዘርፍ የአመቱን ምርጦች ይፋ አድርጓል። በአሰልጣኞች ዘርፍ ኢትዮጵያዊው አሰልጣኝ ሁሴን ሺቦ የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሆነው ተመርጠዋል። ከዚህ ባለፈም አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ እና አትሌት ለሜቻ ግርማ ደግሞ በሁለቱም ጾታዎች የአመቱ ምርጥ ወጣት አትሌት ዘርፍ…

ኢትዮጵያ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና እና ደቡብ አፍሪካ ጋር ተደልድላለች

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለ2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ድልድል ተጋጣሚዎች ተለይተዋል። የማጣሪያ የምድብ ድልድሉ ትናንት ይፋ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ በምድብ 7 ተደልድላለች። በምድቡ ጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባብዌ የኢትዮጵያ ተጋጣሚዎች ሆነዋል። በማጣሪያው የየምድቦቹ አሸናፊዎች በዕጣ ድልድል እርስ…

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የቡሩንዲ አቻውን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታየቡሩንዲ አቻውን አሸነፈ፡፡ በኮስታሪካ እና ፓናማ አዘጋጅነት ለሚካሄደው 10ኛው የሴቶች ከ20 አመት በታች አለም ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ ቡጁምብራ ላይ ከቡሩንዲ ጋር አድርጎ 5 ለ 0…

ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን ከኪፕቾጌ ጋር ይፎካከራል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀነኒሳ በቀለ ሚያዚያ ወር ላይ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን ከኬንያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌ ጋር እንደሚሮጥ አስታወቀ። ቀነኒሳ ከኪፕቾጌ ጋር ዳግም ለመወዳደር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል። ውድድሩን አስመልክቶ በሰጠው አስተያየትም በውድድሩ የተሻለ ነገር ለማድረግ ጥሩ መስራ መስራቱንም ነው የተናገረው። ጉዳት ባለፉት አመታት…

የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ጥር ወር ላይ እንደሚካሄድ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ጥር ወር ላይ እንደሚካሄድ አስተናጋጇ ካሜሮን ገለፀች። ትናንት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) እና የካሜሮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያካሄዱትን ስብሰባ ተከትሎ የካፍ ፕሬዚዳንት የአፍሪካ ዋንጫ ከፈረንጆፐቹ ጥር 1 እስከ 29 ድረስ እንደሚካሄድ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል። የአፍሪካ ዋንጫ…

ወላይታ ድቻ የቀድሞ አሰልጣኙ ወደ ስራ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ጥር 7፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለብ የቀድሞ አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ወደ ስራ እንዲመለሱ ጥሪ አቀረበ። ክለቡ አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ በ8ኛ ሳምንት በሜዳቸው ላይ መሸነፋቸውን ተከትሎ በስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙበትን ማስረጃ በመያዝ ወደ ምድብ ስራቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማቅረቡን አስታውቋል። ክለቡ በቀጣይ ከጅማ አባጅፋር…