Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አንጋፋው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢ ብሪያንትና የ13 ዓመት ልጁ በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወታቸው አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ኮቢ ብሪያንት ከልጁ ጂያና ጋር በሄሊኮፕተር አደጋ ህይወቱ አለፈ። ካሊፎርኒያ ካላባሳስ ከተማ በተከሰተው የሄሊኮፕተር አደጋ ኮቢ ብሪያንት እና ልጁን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል። የ41 ዓመቱ ኮቢ ብሪያንት በግል ሄሊኮፕተር እየተጓዘ በነበረበት ወቅት ሄሊኮፕተሩ ተከስክሶ መቃጠሉን ፖሊስ አስታውቋል። በደረሰው አደጋ በህይዎት የተረፈ ሰው እንደሌለም ተጠቁሟል። የአምስት ጊዜ የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ማህበር ሻምፒዮኑ ብሪያንት ለሎስአንጀለስ…
Read More...

ዩጋንዳ የኢትዮጵያ የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድንን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በህንድ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም የሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዋንጫ ውድድር ለማለፍ ሲያደርግ ከነበረው ቅድመ ማጣሪያ ውጪ ሆነ፡፡ ብሄራዊ ቡድኑ በዛሬው ዕለት በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም የዩጋንዳ አቻውን አስተናግዶ 3 ለ 1 ተሸንፎ ነው ከቅድመ ማጣሪያ ውጪ…

በፕሪምየር ሊጉ አራት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በአዲስ አበበ እና በክልል ከተማዎች ተካሂደዋል፡፡ ፋሲለደስ ስታድየም ላይ ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ 1 ለ 0 በማሸነፍ በ18 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ መቀመጥ ችሏል፡፡ አዳማ ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን አስተናግዶ 2 ለ 0 ያሸነፈ ሲሆን በዚህም በሁለት…

37ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 17፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 37ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ውድድር በዛሬው ዕለት ተካሄደ፡፡   የተካሄዱት የውድድሮች ርቀትም የ10ኪ.ሜ አዋቂ ሴቶች ፣ 6 ኪሎ ሜትር ወጣት ሴቶች ፣ የ8 ኪሜ የወጣት ወንዶች ፣ 10 ኪሎ ሜትር ወንዶች ፣ ድብልቅ ሪሌ እና ቬትራን ናቸው፡፡   በዚህም በ10ኪሎ ሜትር አዋቂ…

በፕሪምየር ሊጉ ሰበታ ከተማ እና ወላይታ ድቻ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል። ሰበታ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ሰበታ ከተማ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የሰበታ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ፍፁም ገብረማርያም እና አዲስ ተስፋዬ ሲያስቆጥሩ፥የሃዋሳ ከተማን ብቸኛ ግብ…

36ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ነገ ይካሄዳል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 37ኛው የጃን ሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ነገ በጃንሜዳ ይካሄዳል። በውድድሩ አምስት ክልሎች፣ ሁለት የከተማ አስተዳደሮች፣ 37 ክለቦች እና የማሰልጠኛ ተቋማት የሚሳተፉ ይሆናል። 6 ኪሎ ሜትር ወጣት ሴቶች ፤ በ10 ኪሎ ሜትር አዋቂ ሴቶች፣ በወንዶች 8 ኪሎ ሜትር ወጣት ወንዶች፣ በ10 ኪሎ ሜትር አዋቂ…

ጠ/ሚ ዐቢይ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት ከተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበጃፓን ቶኪዮ ለሚካሄደው ኦሊምፒክ የሚደረጉ ዝግጅቶችን ለማስተባበር ከተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ። በውይይቱ ወቅት ኮሚቴው ለቶኪዮ ኦሊምፒክ እያደረገ ያለውን ዝግጅት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል። በውድድሩ ከተሳትፎ ባለፈ አትሌቶች በድል እንዲመለሱ የማገዝ አላማ እንዳለው መግለጹን…