Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ ስታዲየም ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 5 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። የመጀመሪያዋን ጎል በ21ኛው ደቂቃ ላይ ሀብታሙ ገዛኸኝ ሲያስቆጥር፥ በ59 እና በ70ኛው ደቂቃ አዲስ ግደይ ኳሷን ከመረብ አገናኝቷል። በ66ኛው ደቂቃ ደግሞ ይገዙ ቦጋለ አራተኛውን ጎል ያስቆጠረ ሲሆን፥ በ69 ደቂቃ…
Read More...

የ2020 የቤት ውስጥ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኮሮና ቨይረስ ምክንያት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና አስተናጋጅነት በናንጂንግ ሊካሄድ የነበረውን የ2020 የቤት ውስጥ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሀገሪቱ በተከሰተው በኮሮና ቨይረስ ምክንያት መራዘሙ ተገለፀ። የ2020 የቤት ውስጥ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በቻይናዋ ናንጂንግ ከተማ አስተናጋጅነት ከፊታችን ከመጋቢት 4 እስከ መጋቢት 6 ድረስ እንደሚካሄድ ነበር…

በፕሪሚየር ሊጉ መቐለ 70 እንደርታ መሪነቱን ያጠናከረበትን ውጤት አስመዝግቧል

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በክልል ከተሞች እና በአዲስ አበባ ተካሂደዋል። የፕሪሚየር ሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ መቐለ ላይ ከስሑል ሽረ ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል። ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ፋሲል ከነማ ወደ ጅማ አቅንቶ ከጅማ አባ ጅፋር ጋር 0…

ማንቼስተር ዩናይትድ እና ስፖርቲንግ ሊዝበን በብሩኖ ፈርናንዴዝ ዝውውር ተስማምተዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥር ወር የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሊዘጋ ሁለት ቀናት ቀርተውታል። ክለቦችም ራሳቸውን ለማጠናከር በዝውውር መስኮቱ እየተሳተፉ ይገኛል። ለረጅም ጊዜያት የፖርቹጋላዊው አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ፈላጊ ሆኖ የቆየው የእንግሊዙ ማንቼስተር ዩናይትድ ፍላጎቱን ለማሳካት ተቃርቧል። የላንክሻየሩ ክለብ ከፖርቹጋሉ ስፖርቲንግ…

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የልዩ ኦሊምፒክ ውድድር 3 ሜዳሊያዎችን አገኘች

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በግብፅ ካይሮ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ልዩ ኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ 3 ሜዳሊያዎች አገኘች። የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ስፖርተኞች የሚሳተፉበት የአፍሪካ የልዩ ኦሊምፒክ ውድድር በካይሮ በአትሌቲክስ፣ በእግር ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ እና በቦሽያ ስፖርት እየተካሄደ ይገኛል። ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ስፖርት በአራት…

ለቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ዝግጅትና ተሳትፎ 1 ቢሊየን ብር የመሰብሰብ ግብ ተቀምጧል

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትና ተሳትፎ አንድ ቢሊዮን ብር የመሰብሰብ ግብ መቀመጡን የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ገለጸ። ኮሚቴው ዛሬ የቶኪዮ 2020 ኦሎፒክ ዝግጅትን በተመለከተ የሚጠበቁ ተግባራትን አስመልክቶ ውይይት አካሂዷል። በዚሁ መሰረት ኮሚቴው የሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። በውይይቱ…

የከተማ አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የስታዲየም መገንቢያ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለቦች የስታዲየም መገንቢያ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሰጠ። የስታዲየም እና የስፖርት ማዕከል መገንቢያ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታውን ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለቦች ማስረከባቸውን የከተማ…