Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ማንቼስተር ሲቲ ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ለሁለት አመት ታገደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ማንቼስተር ሲቲ ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እንዳይሳተፍ ታገደ። ክለቡ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበርን የገንዘብ አስተዳደር (የፋይናንሺያል ፌር ፕሌይን) አላከበረም በሚል ነው እገዳው የተጣለበት። እገዳውን ተከትሎም ክለቡ በቀጣዮቹ ሁለት አመታት በትልቁ የክለቦች ውድድር አይሳተፍ፤ ይህም ክለቡን እስከ 170 ሚሊየን ፓውንድ ያሳጣዋል ተብሏል። የአሁኑ እገዳ ከፈረንጆቹ 2012 እስከ 2016 ክለቡ ከስፖንሰር ሺፕ ገቢ አገኘሁት በሚል ለእግር…
Read More...

ውጤት ላስመዘገቡ አትሌት እና አሰልጣኞች ሽልማት ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2012 ኤፍ.ቢ.ሲ) በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ውጤት ያስመዘገቡ አትሌቶች እና ባለሙያዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተላቸው። የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማቱ በ17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ በ12ኛው መላ አፍሪካ ጨዋታዎች፣ በ6ኛው የአፍሪካ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ሻምፒዮን፣ በ1ኛው የአፍሪካ መስማት የተሳናቸው አትሌቲክስ…

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና እና ወልቂጤ ከተማ አቻ ተለያዩ  

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት የመጨረሻ መርሃ ግብር ጨዋታ ዛሬ ተካሂዷል። በዚህም ኢትዮጵያ ቡና እና ወልቂጤ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ ግብ ፍቅረየሱስ ተክለብርሀን በ29ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል። የወልቂጤ ከተማን ግብ…

የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ሞገስ ታደሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋች ሞገስ ታደሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ሞገስ ባጋጠመው የጤና እክል ሳቢያ በየካቲት 12 ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ሞገስ ታደሰ በአዳማ ከተማ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በሲዳማ ቡና፣ በወልዲያ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ…

አትሌት ሳሙኤል በአንድ ማይል የ2020ን ሁለተኛ ፈጣን ሰዓት አስመዘገበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አትሌት ሳሙኤል ተፈራ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት በአንድ ማይል ርቀር ሩጫ ሁለተኛውን የዓለም ፈጣን ሰዓት አስመዘገበ። በትናንትናው ዕለት በአየርላንድ አትሎን የአንድ ማይል የቤት ውስጥ ውድድር ተካሂዷል። አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ርቀቱን በ3 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ86 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ…

በፕሪሚየር ሊጉ ወላይታ ድቻ ሃድያ ሆሳዕናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት የቀኑ ብቸኛ ጨዋታ በሃዋሳ ከተማ ስታዲየም ዛሬ ተካሂዷል። በዚህም ወላይታ ድቻ ሃድያ ሆሳዕናን  1 ለ 0 በሆነ ውጤት  አሸንፏል። የወላይታ ድቻን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ደጉ ደበበ ከመረብ አገናኝቷል። የጨዋታውን ውጤት ተከትሎ ወላይታ ድቻ በፕሪሚየር ሊጉ 8ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ…

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አንድ ጨዋታ ተካሄዷል። በሜዳው አዳማ ከተማን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና ጨዋታውን 3 ለ 2 ማሸነፍ ችሏል። የማሸነፊያ ጎሎችን አማኑኤል እንዳለ፣ ዳዊት ተፈራ እና ሀብታሙ ገዛኸኝ ማስቆጠር ችለዋል።