Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የእንግሊዝ የሃገር ውስጥ እግር ኳስ ውድድሮች ተራዘሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር የሚያስተዳድራቸው ውድድሮች እስከ መጭው ሚያዚያ ወር መጨረሻ ድረስ ተራዘሙ። የእንግሊዝ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል የፕሪሚየር ሊጉን ጨምሮ በሌሎች የሃገር ውስጥ ውድድሮች ቀጣይ ሁኔታ ላይ በዛሬው እለት ከክለቦች ጋር ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። በውሳኔው መሰረትም ፕሪሚየር ሊጉን ጨምሮ…

አትሌት ብርሃኑ ፀጉ ለአራት ዓመታት ከውድድር ታገደ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ብርሃኑ ፀጉ የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም መጠቀሙ በመረጋገጡ ለአራት ዓመታት በማንኛውም ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ ተጥሎበታል። አትሌት ብርሃኑ ባለፈው መስከረም ወር ዴንማርክ ኮፐንሀገን በተካሄደው የግማሽ ማራቶን የግል ውድድር ላይ የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም በመጠቀም ተጠርጥሮ ለሰባት ወራት…

የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ለ1 ዓመት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዘንድሮ 2020 ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የ2020 አውሮፓ እግር ኳስ ዋንጫ ለ1 ዓመት እንዲራዘም ተወሰነ። የዘንድሮ የአውሮፓ ዋንጫ በአውሮፓውያኑ ከሰኔ 2020 ጀምሮ ለአንድ ወር እንደሚካሄድ መርሃ ግብር ወጥቶ ነበር። ሆኖም ግን በኮሮናቫይረስ ምክንያት የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ለ1 ዓመት እንዲራዘም የአውሮፓ እግር ኳስ…

በሀገር ውስጥ የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች እና ጨዋታዎች ለ15 ቀናት እንዳይካሄዱ ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን በሀገር ውስጥ የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች፣ ጨዋታዎች፣ የስፖርት ፌስቲቫል፣ ስልጠናዎች፣ ጉባኤዎች እና ትላልቅ ስብሰባዎች ለ15 ቀናት በየትኛውም ቦታ እንደማይካሄዱ አስታወቀ። ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ውድድሮች እና የስልጠና መድረኮች ለህዝቡ ደህንነት ሲባል በቫይረሱ ዙሪያ ተጨማሪ…