Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ዝላታን ኢብራሂሞቪች የኤሲ ሚላን የቦርድ አባል ለመሆን መስማማቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ስዊድናዊው አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች የጣሊያኑን ኤሲ ሚላን በቦርድ አባልነት ለመቀላቀል መስማማቱ ተገልጿል፡፡ እስከ 41 ዓመቱ ድረስ በኢንተርናሽናል እግር ኳስ የዘለቀው ግዙፉ አጥቂ ባለፈው ክረምት ራሱን ከእግር ኳስ ዓለም ማግለሉ የሚታወስ ነው፡፡ ከእግር ኳሱ ከተገለለ በኋላ ከክለቡ ጋር ግንኙነቱን ያላቋረጠው ኢብራሂሞቪች ለሶሰተኛ ጊዜ ከኤሲ ሚላን ጋር ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡ ዝላታን በክለቡ በይፋ ስራ ለመጀመር በሚቀጥሉት ወራት ሪፖርት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Read More...

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ወደ አሸናፊነት ሲመለስ ዌስትሃም በሰፊ የጎል ልዩነት ተሸንፏል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ሶስት ጨዋታዎች ተደርገዋል። 11 ሰአት ላይ በተደረጉት ጨዋታዎች ኤቨርተን ከቼልሲ፣ ፉልሃም ከዌስትሃም ዩናይትድ እንዲሁም ሉተን ታዎን ከማንቼስተር ሲቲ ጋር ተገናኝተዋል። ከፋይናንስ ህግ ጥሰቶች ጋር በተያያዘ 10 ነጥቦች የተቀነሱበት የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን…

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል ቀንቶታል፡፡ ዛሬ 9፡00 ሰአት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስቴዲየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸመኔ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የድል ጎሎች ባሲሩ ኡመር እና ሲሞን…

ከጥር ወር ጀምሮ የአበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር ይደረጋል- ባለስልጣኑ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2024ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ ለሚሳተፉ አትሌቶች ከጥር ወር 2016 ጀምሮ የአበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር ሊያደርግ መሆኑን የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን አስታወቀ። ለፓሪስ ኦሊምፒክ ለሚሳተፉ አትሌቶችም ከወዲሁ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ነው የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬከተር መኮንን ይደርሳል…

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አሸናፊ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ የስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት አሸናፊ ሆናለች፡፡ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ቡዳፔስት ላይ በተካሄደ የ10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ትውልደ ኢትዮጵያዊት የሆነችው እና በአሁኑ ጊዜ ለሆላንድ የምትሮጠው ሲፋን ሐሰን በሩጫ ወቅት መውደቋ ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎም…

በፕሪሚየር ሊጉ መቻል እና ባህር ዳር ከተማ ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 28 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰባተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው እለት ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።   ቀደም ብሎ በተካሄደ ጨዋታ መቻል ከአዳማ ከተማ ተገናኝተዋል።   አዳማ ከተማ ጨዋታውን በቢኒያም አይተን ጎል 1 ለ 0 መምራት ቢችልም ተከታትለው በተቆጠሩበት ሁለት ጎሎች 2 ለ 1…

በፕሪሚየር ሊጉ ወላይታ ድቻ እና ወልቂጤ ከተማ ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ የመጀመሪያው ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ ሀምበርቾን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የወልቂጤ ከተማ ግብን አሜ መሐመድ ያስቆጠረ ሲሆን÷በዚህም ቡድኑ ተከታታይ ድልን አሳክቷል። እንዲሁም 12 ሠዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ…