Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በሬድዮ በቀጥታ ለማስተላለፍ ለሚፈልጉ ድርጅቶች ሊሸጥ ነው

አዲስ አበባ ፣ዻጉሜን 5 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ በ2013 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን  የፕሪሚየር ሊግ ውድድር  በሬድዮ የቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ ለሚፈልጉ የሚዲያ ተቋማት ሊሸጥ መሆኑን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ለመምራት የተቋቋመ ህጋዊ ተቋም ነው ፡፡ በመሆኑም  ካምፓኒው በቀጣይ የሚካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በቀጥታ የሬድዮ ስርጭት ለማስተላለፍ የሚያስችለውን መብት፣  ህጋዊ ፍቃድ ላላቸው የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ሚዲያ…
Read More...

ሞ ፋራህ በኃይሌ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሸለ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ብሪታኒያዊው ሞ ፋራህ ብሩሴልስ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ለ13 ዓመታት በሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ተይዞ የቆየውን ክብረ ወሰን አሻሻለ፡፡ በትውልድ ሶማሊያዊው የሆነው ሞ ፋራህ በአንድ ሰዓት ውስጥ 23 ነጥብ 33 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ነው በኃይሌን ተመዝግቦ የነበረውን 21 ነጥብ 285…

በስፖርታዊ ጨዋታዎች እና ውድድሮች የአደረጃጀት እና የአሠራር ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 28 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በስፖርታዊ ጨዋታዎች እና ውድድሮች የአደረጃጀት እና የአሠራር ረቂቅመመሪያ ላይ ውይይት ተካሂዷል። በኢትዮጵያ በተለያየ ደረጃ የተለያዩ ውድድሮች እና ጨዋታዎች የሚዘጋጁ ሲሆን ÷የሚዘጋጁት ውድድሮች በተደራሽነት ፣ በጥራት ፣በውጤት እና በፍትሐዊነት ደረጃ ጉድለቶች ያሉባቸው መሆኑን የስፖርት ሪፎርም ጥናቱ ማመላከቱ ተገልጿል፡፡…

በአዲስ አበባ የሚገኙ የስፖርት ማህበረሰብ አባላት ለ20 ሺህ ተማሪዎች ጫማ ለመለገስ ቃል ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 27 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የስፖርት ማህበረሰብ አባላት ለ20 ሺህ ተማሪዎች ጫማ ለመለገስ ቃል ገብተዋል። ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የስፖርት ማህበረሰብ አባላት 'አንድ ጫማ ለአንድ ተማሪ' በሚል ባዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ እና ቃልኪዳን ማስገቢያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተዋል። የስፖርት ቤተሰቡ በእለቱ ብቻ 8…

ቼልሲ ቲያጎ ሲልቫን አስፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው ተከላካይ ቲያጎ ሲልቫ የእንግሊዙን ቼልሲ ተቀላቀለ፡፡ ሲልቫ ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ የማራዘም አማራጭ ያለው የአንድ አመት የኮንትራት ፊርማውን አኑሯል፡፡ የ35 አመቱ ተከላካይ ሰማያዊዎቹን በነጻ ዝውውር ከፈረንሳዩ ፒ ኤስ ጂ ተቀላቅሏል፡፡ ሲልቫ በዘንድሮው ክረምት የቼልሲ አራተኛው ፈራሚ ሆኗል፡፡…

ባየር ሙኒክ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ለ6ኛ ጊዜ አነሳ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጀርመኑ ባየር ሙኒክ የፈረንሳዩን ፓሪስ ሴንት ጀርመንን በመርታት ቻምፒየንስ ሊጉን ለ6ኛ ጊዜ አንስቷል። የ2019/2020 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ትናንት ምሽት በፖርቹጋል ዋና ከተማ ሊዝበን ተካሂዷል። በፍፃሜው የጀርመኑ ባየር ሙኒክ ከፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጀርመን የተገናኙ ሲሆን፦ ባየር ሙኒክ…

ሴቪያ የዩሮፓ ሊግ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩሮፓ ሊግ ትናንት ምሽት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ በጀርመን ኮሎኝ የተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ የስፔኑን ሴቪያ ከጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ተገናኝተው ሴቪያ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል፡፡ በጨዋታው ኢንተር ሚላን በሮሜሉ ሉካኩ የፍጹም ቅጣት ምት ጎል ቀዳሚ መሆን ችሎ ነበር፡፡ ይሁን እንጅ ደ ዮንግ…