Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል። ከቀትር በኋላ በተካሄደ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ድሬዳዋ ከተማን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ጎሎች ጌታነህ ከበደ እና ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ አስቆጥረዋል፡፡ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና ሃዋሳ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል። የድል ጎሎቹን መስፍን ታፈሰ ሲያስቆጥር አቤኔዘር ዮሐንስ ደግሞ የሐዋሳ ከተማን የማስተዛዘኛ ጎል አስቆጥሯል።…
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስና መቻል አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ የተለያዩ ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ 12 ሰዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስና መቻል በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ያካሄዱት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስን ብቸኛ ግብ አቤል ያለው ሲያስቆጠር ÷ የመቻልን ደግሞ ምንይሉ…

ሽመልስ በቀለ ራሱን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማግለሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስመር አጥቂው ሽመልስ በቀለ ከ15 ዓመታት በላይ የብሔራዊ ቡድን ግልጋሎት በኋላ ራሱን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማግለሉን ይፋ አድርጓል። የመስመር አጥቂው የእግር ኳስ ጅምሩን ሀዋሳ ከተማ ያደረገ ሲሆን÷ በኋላም በቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይታ አድርጎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ክብርን ከክለቡ ጋር አሳክቷል፡፡ ከሀገር ውጪም …

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና ተጋጣሚዎቻቸውን ረቱ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ9ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ 9፡00 ላይ ኢትዮጵያ መድንን የገጠመው ሲዳማ ቡና በይገዙ ቦጋለ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም ሲዳማ ቡና ነጥቡን ወደ 11 ከፍ በማድረግ 7ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ÷ ኢትዮጵያ መድን ደግሞ በነበረበት 8ኛ…

ዋይኒ ሩኒ ከበርሚንግሃም አሰልጣኘነቱ ተሰናበተ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ በርሚንግሃም ሲቲ ዋይኒ ሩኒን ከአሰልጣኝነት አሰናበተ። በእንግሊዝ ቻምፒዮን ሺፕ እየተሳተፈ የሚገኘው በርሚንግሃም ሩኒን ባለፈው ጥቅምት ወር በዋና አሰልጣኝነት መቅጠሩ ይታወሳል። አሁን ላይ ክለቡ የገባበትን የውጤት ቀውስ ተከትሎም የ38 አመቱን የቀድሞ የማንቼስተር ዩናይትድ እና እንግሊዝ…

የሜሲ10 ቁጥር መለያ በሌላ ተጫዋች እንደማይለበስ አርጀንቲና አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊዮኔል ሜሲ እግር ኳስ ካቆመ በኋላ 10 ቁጥር መለያው በሌላ ተጫዋች ሊለበስ እንደማይችል የአርጅንቲና እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ክላውዲዮ ታፒያ÷የሊዮኔል ሜሲ10 ቁጥር መለያ ለዘላለም ተከብሮለት ይኖራል፤እኛ ለእርሱ የምናደርግለት ትንሹ ነገር ይህ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ሜሲ ሀገሩ አርጀንቲና…

ኡጋንዳዊው አትሌት በኬንያ መኪና ውስጥ ሕይወቱ አልፎ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኡጋንዳዊው አትሌት ቤንጃሚን ኪፕላጋት በኬንያ መኪና ውስጥ ሕይወቱ አልፎ መገኘቱ ተሰምቷል፡፡ በሶስት የኦሎምፒክ ውድድሮች በ3 ሺህ መሰናክል ሀገሩን የወከለው አትሌት ኪፕላጋት አንገቱና ደረቱ ላይ በስለት ተወግቶ ሕይወቱ ማለፉን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ የ34 ዓመቱ ኪፕላጋት ታዋቂ አትሌቶች ልምምድ በሚያደርጉባት…