Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አትሌት ሃጎስ በጣልያን በተካሄደ የ10 ሺህ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጣልያን በተካሄደ የ10 ሺህ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት ሃጎስ ገብረህይወት የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸናፊ ሆኗል፡፡ አትሌት ሃጎስ ርቀቱን 29 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸንፏል፡፡ የቀድሞው የቦታው ክብረ ወሰን 30 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ እንደነበር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ…

ዋልያዎቹ በቀጣይ ሳምንት ከዛምቢያ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በቀጣይ ሳምንት ከዛምቢያ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።   የወዳጅነት ጨዋታው ጥቅምት 12ና 15 ቀን 2013 በአዲስ አበባ ስታድየም እንደሚካሄድ ነው የተገለፀው።   ብሄራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ…

የኮማንደር አሰልጣኝ ሁሴን ሽቦ “አዳኙ አሰልጣኝ” መጽሃፍ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮማንደር አሰልጣኝ ሁሴን ሽቦ "አዳኙ አሰልጣኝ" መጽሃፍ በዛሬው እለት ተመርቋል። በመጽሃፉ ምረቃ ላይም የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ኃላፊዎች ተገኝተዋል።…

በፖላንድ የዓለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶችም በሴቶችም 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶችም በሴቶችም 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል። በወንዶች በተካሄደው የዓለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ኢትዮጵያው አትሌት አምደወርቅ ዋለልኝ 59 ደቂቃ 08 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት 3ኛ ደረጃ ይዞ ውድድሩን ማጠናቀቅ ችሏል።…

በስፖርት አመራርነት የሚታወቁት አቶ ያሚ ከበደ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ውስጥ በስፖርት አመራርነት እጅግ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው አቶ ያሚ ከበደ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡   አቶ ያሚ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ66 ዓመታቸው በትናንትናው ዕለት ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት፡፡   አቶ ያሚ ስራ ከጀመሩበት…