Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹ በኒጀር አቻቸው 1 ለ 0 ተሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹ በኒጀር አቻቸው 1 ለ 0 ተሸነፉ:: የኢትዮጵያ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት ከኒጀር ጋር በኒያሚው ስታድ ጀነራል ሴኒ ስታዲየም አድርገዋል፡፡ በጨዋታው ኒጀሮች ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት በማስቆጠር አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ አይቮሪ ኮስት ከማዳጋስካር ያደረጉት ጨዋታ በአይቮሪኮስት 2 ለ 1 አሸናፊነት መጠናቀቁ የሚታወስ ነው።
Read More...

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር  ዶክተር ሂሩት ካሰው በአዲስ አበባ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ብሔራዊ ስታዲየም ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር  ዶክተር ሂሩት ካሰውን  ጨምሮ ከፍተኛ የስፖርት አመራሮች በአዲስ አበባ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ብሔራዊ ስታዲየም ጎብኝተዋል ፡፡ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ገርጂ አካባቢ በቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ስራ ተቋራጭነት በኤም ኤች ኢንጅነሪንግ አማካሪነት…

ዋልያዎቹ በወዳጅነት ጨዋታ ከሱዳን ጋር አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በወዳጅነት ጨዋታ ከሱዳን አቻው ጋር ተጫውቷል፡፡   ማምሻውን በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡   የመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታው ክፍለ ጊዜ ጌታነህ ከበደ ባስቆጠራት ጎል በዋልያዎቹ መሪነት ቢጠናቀቅም ሱዳኖች በተከታታይ…

ሎዛ አበራ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ፈረመች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሎዛ አበራ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ፈረመች፡፡ የቡድኑ አሰልጣኝ አቶ ብርሀኑ ግዛው ለረጅም ጊዜ ሲከታተሏት እንነበር ገልጸው ተጫዋቿ ቡድናቸውን በመቀለቀሏ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ሎዛ አበራ በበኩሏ ቡድኑን በመቀላቀሏ መደሰቷንና ከሌሎች የቡድን አጋሮቿ ጋር በመሆን ውጤታማ ለመሆን…

የኦሊምፒክ ተሳታፊ  አትሌቶች ከህዳር 1 እስከ 13 ሊዘከሩ ነው

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 26 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሊምፒክ ተሳታፊ ጀግና አትሌቶች ከህዳር 1 እስከ 13  ቀን 2013 ዓ. ም. ድረስ በየተሳተፉባቸው ኦሊምፒኮች ቅደም ተከተል መሠረት ቀን ተሰይሞላቸው እንደሚዘከሩ ተገለጸ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሻምበል አትሌት አበበ ቢቂላን 60ኛ ዓመት የሮም ኦሊምፒክ የማራቶን ድል ምክንያት በማድረግ  ከሜልቦርን እስከ ሪዮ…

አሰልጣኝ እንድርያስ ብርሃኑ የኢትዮጵያ ከ17ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ እንድርያስ ብርሃኑ የኢትዮጵያ ከ17ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ መድን የቀድሞ ከ17 ዓመት በታች እና የአሁን ከ20ዓመት በታች አሰልጣኝ እንድርያስ ብርሃኑን የኢትዮጵያ ከ17ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን  ዋና አሰልጣኝ በማድረግ  …

የሩጫ እና ብስክሌት ቅብብል ውድድር በእንጦጦ ፓርክ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሩጫ እና ብስክሌት ቅብብል ውድድር በእንጦጦ ፓርክ እንደሚያካሂድ አስታወቀ። ውድድሩ በቀጣዩ ወር መግቢያ ይደረጋል ነው የተባለው። በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው ውድድር በአንድ ቡድን አራት ሰዎች እንደሚካፈሉበት ይጠበቃል። ከአራቱ ሰዎች ሁለቱ ብስክሌተኞች፣ቀሪዎቹ ሁለቱ ደግሞ ሯጮች…