ስፓርት
ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ራምኬል ጀምስ እና አማኑኤል አድማሱ አስቆጥረዋል፡፡
የዛሬው የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ÷ ምሽት 12 ሰዓት ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ሊጉን ኢትዮጵያ መድን በ60 ነጥብ ሲመራ÷ ኢትዮጵያ ቡና በ51 ነጥብ ይከተላል፡፡
ወራጅ ቀጣና ላይ…
Read More...
አርሰናል ከኒውካስል ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ አርሰናል ኒውካስል ዩናይትድን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ምሽት 12:30 በሚደረገው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፏቸውን ለማረጋገጥ ጠንካራ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ ቀን 10:15…
ሸገር ከተማ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አስቀድሞ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ማደጉን ያረጋገጠው ሸገር ከተማ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ አሸናፊ ሆኗል፡፡
የከፍተኛ ሊጉ የ26ኛ ሳምንት እና የውድድር ዓመቱ የማጠቃለያ መርሐ ግብሮች የተደረጉ ሲሆን÷ ቀን 8 ሰዓት ላይ ሸገር ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና 3 አቻ ተለያይተዋል።
ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ…
ክሪስታል ፓላስ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን አነሳ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኤፍኤ ካፕ የፍጻሜ ዋንጫ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ ማንቼስተር ሲቲን በማሸነፍ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን አንስቷል፡፡
በግዙፉ የእንግሊዝ ዌምብሌይ ስታዲየም የተካሄደውን የኤፍኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የፔፕ ጓርዲዮላ ቡድን ከፍተኛ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ የነበረው ቢሆንም…
ኢትዮጵያ መድን መቐለ 70 እንደርታን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን መቐለ 70 እንደርታን 1 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ አቡበከር ሳኒ የኢትዮጵያ መድንን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡
ውጤቱን ተከትሎም ኢትዮጵያ መድን ነጥቡን ወደ 60 ከፍ በማድረግ ለዋንጫ…
የኤፍኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኤፍኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ከክሪስታል ፓላስ ዛሬ ምሽት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
የፍጻሜ ጨዋታው ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ በእንግሊዝ ዌምብሌይ ስታዲየም ነው የሚካሄደው፡፡
ውሃ ሰማያዊዎቹ ለ8ኛ ጊዜ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ የሚገቡ ሲሆን÷ክሪስታል ፓላሶች ደግሞ በታሪክ ለመጀመሪያ…
ሀዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ30ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የሀዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች እስራኤል እሸቱ እና አሊ ሱሌማን ሲያስቆጥሩ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ቢኒያም ፍቅሬ ከመረብ አሳርፏል፡፡
የሀዋሳ ከተማ የፊት መስመር ተጨዋች አሊ ሱሌማን በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን…