Fana: At a Speed of Life!

ስብሃት ነጋን ጨምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዘጠኝ የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋን ጨምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዘጠኝ የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የጥፋት ቡድኑ አመራሮች በቁጥጥር ስር ማዋሉን መግለጹ ይታወሳል።

የጁንታው አመራሮች የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስና ሌሎች የፌደራል ጸጥታ ተቋማት ባደረጉት ፍተሻና አሰሳ ከተደበቁበት ለሰው ልጅ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ሰርጥ ውስጥ  ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

የጥፋት ቡድኑ አመራሮችን ለመከላከል በአካባቢው ጥበቃ ላይ የነበረ የጁንታው ታጣቂ ሀይል መደምሰሱም በወቅቱ ተገልጿል።

በዚሁ መሰረት

1.የጁንታው ቁንጮ አመራርና የጥፋት ስትራቴጂስት፣ ስብሃት ነጋ

2.ቅዱሳን ነጋ -የትግራይ ክልል አፈ ጉባኤ የነበረች

 

  1. ቴዎድሮስ ሀጎስ-የመለስ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንትና የኢፈርት ቦርድ ሃላፊ የነበረ፣

 

  1. አባዲ ዘሙ-በሱዳን የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር የነበረና የጁንታውን ፖለቲካ ክንፍ የተቀላቀለ፣

 

  1. ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ -የቀድሞ የትግራይ ክልል ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣

 

  1. ገብረመድህን ተወልደ-የክልሉ ንግድ ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣

 

  1. ወልደጊዮርጊስ ደስታ-የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበረ፣

 

  1. ተክለወይኒ አሰፋ-የማረት ስራ አስፈጻሚ የነበረ፤

 

  1. ወይዘሮ ምህረት ተክላይ – የክልሉ ምክር ቤት ህግ አማካሪ የነበረች፤ ሁሉም በዛሬው እለት አዲስ አበባ ገብተዋል።

 

የምዕራብ እዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል መሰለ መሰረት  ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የጁንታውን ሃይል ድል አድርጎ አሁን ደግሞ የቡድኑን አመራሮች በቁጥጥር ስር እያወለ መሆኑን ተናግረዋል።

ሰራዊቱ በህግ ማስከበርና ህልውና ዘመቻ አንፀባራቂ ድሎችን ያስመዘገበ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የጥፋት ቡድኑ አመራሮች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ነው የተናገሩት።

የ24ኛ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል አማረ በዓታ በበኩላቸው፣ ሰራዊቱ ሌት ተቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ቀሪ የጁንታው ቡድን አመራሮች ከያሉበት እያደነ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.