Fana: At a Speed of Life!

ምርት ገበያው በጥር ወር 4 ነጥብ 64 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸውን ምርቶችአገበያየ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በጥር ወር 4 ነጥብ 64 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸውን 9 ሺህ 239 ቶን ምርቶች አገበያየ።

ምርት ገበያው በወሩ 43 ሺህ 927 ቶን ሰሊጥ፣ 24 ሺህ 391 ቶን ቡና፣ 9 ሺህ 643 ቶን ቦሎቄ፣ 9 ሺህ 268 ቶን አረንጓዴ ማሾ እንዲሁም 5 ሺህ 9 ቶን አኩሪ አተር ማገበያየቱን ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በወሩ ሰሊጥ 48 በመቶ የግብይት መጠንና 40 በመቶ የግብይት ዋጋ በማስመዝገብ ቀዳሚ ሆኗል።

43 ሺህ 927 ቶን ሰሊጥ በ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ሲገበያይ፥ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በመጠን 37 በመቶና በዋጋ 33 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተገለጸው።

በወሩ 24 ሺህ 391 ቶን ቡና ለገበያ ቀርቦ በ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሲገበያይ፥ ለውጭ ገበያ የቀረበ ቡና 51 በመቶ የግብይት መጠንና ዋጋ በማስመዝገብ ትልቁን ድርሻ ይዟል።

ግብይቱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ወር ጋር ሲነፃፀር በመጠን በ10 በመቶ ሲቀንስ፥ በዋጋ 21 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ከዚህ ባለፈም ለገበያ የቀረበ 9 ሺህ 643 ቶን ነጭ ቦሎቄ በ201 ነጥብ 17 ሚሊየን ብር ሲገበያይ ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር በመጠንም ሆነ በዋጋ ጭማሪ አሳይቷል ነው ያለው።

9 ሺህ 268 ቶን አረንጓዴ ማሾ በ240 ሚሊየን ብር እንዲሁም 5 ሺህ 9 ቶን አኩሪ አተር በ65 ነጥብ 58 ሚሊየን ብር ማገበያየቱንም ነው ምርት ገበያው ያስታወቀው።
የምርቶቹ ግብይት ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር በመጠንም ሆነ በዋጋ ጭማሪ ማሳየቱንም ምርት ገበያው ገልጿል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.