የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 30 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥቅምትና ህዳር ወር የነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ ጭማሪ ማድረጉን የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም መሰረት ቤንዚን በሊትር 20 ብር ከ28 ሳንቲም ፣ ነጭ ናፍታ በሊትር 17 ብር ከ75 ሳንቲም ፣ ኬሮሲን በሊትር 15 ብር ፣ ቀላል ጥቁር ናፍታ 15 ብር ከ75 በሊትር ፤ ከባድ ጥቁር ናፍታ 15 ብር ከ15 ሳንቲም በሊትር ፣ የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 22 ብር ከ01 ሳንቲም እንዲሆን መወሰኑን ነው ሚኒስቴሩ በላከው መግለጫ ያመለከተው ።
Comments

Name *
Submit Comment