የሀገር ውስጥ ዜናዎች (9803)

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአስተዳደር እና የጸጥታ ስራዎች በሃገሪቱ የልማት አንቅስቃሴ ላይ ምንም አይነት ተጽእኖ ሳይፈጥሩ የተቀመጡ ግቦችን ሙሉ ለሙሉ ለማሳካት በቀጣይ ርብርብ እንደሚደረግ የፌደራል ጉዳዮች ሚንስትር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ተናገሩ።

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሱዳን የታላቁ ህዳሴ ግድብ የምትደግፈው "ለፖለቲካዊ ፍጆታ ሳይሆን ግድቡ ለሱዳን ህዝቦች በሚኖረው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ነው" ሲሉ በኢትዮጵያ የአገሪቱ አምባሳደር ገለጹ።

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከአዲስ አበባ ተግባረ እድ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ የተመረቁ አንዳንድ ሰልጣኞች ወቅቱን የጠበቀ የሙያ ብቃት ምዝና ማረጋገጫ (ሲ.ኦ.ሲ) ባለመውሰዳቸው በጊዜ ስራ ለማግኘት መቸገራቸውን ተናገሩ።

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አዳማ ከተማን በአዲስ አደረጃጀት ሞዴል የሚያደርጋት እቅድ ተዘጋጀ።