የሀገር ውስጥ ዜናዎች (9397)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ተጭኖ በሚጓጓዝ የዳሽን ቢራ ምርት ላይ፥ በተከዜ ድልድይ እና አዲ አርቃይ ከተማ የሚገኝ የመንገድ ፕሮጀክት ካምፕ እና በሌሎች ፕሮጀክት ላይ ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር የዋሉ አራት ተከሳሾች ክስ ቀረበባቸው።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት ትልቅ ሚና እንዲጫወት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ፥ ከሱዳን ፕሬዝዳንት ኡመር ሀሰን አልበሽር የሱዳን ከፍተኛ ወታደራዊ ኒሻን ተበረከተላቸው።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በመንግስታቱ ድርጅት መዋቅር ማሻሻያ ዙሪያ ትናንት በተደረገ የከፍተኛ ደረጃ ምክክር ተሳትፈዋል።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአከራይ እና ተከራይ መካከል የሚያጋጥመውን የእርስ በእርስ ግጭት የሚፈታና በቤት ኪራይ ተመን ውስጥ የደላሎችን ጣልቃ ገብነት ያስቀራል የተባለ ረቂቅ አዋጅ በዚህ ዓመት ፀድቆ ወደ ስራ ይገባል ተባለ።