የሀገር ውስጥ ዜናዎች (8511)

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው 1438ኛው የረመዳን ወር በሁሉም የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በነገው እለት እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የግንቦት 20 ድሎችን በጥልቅ ተሃድሶ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፊታችን እሁድ የሚከበረውን 26ኛውን የግንቦት 20 የድል በዓልን ምክንያት በማድረግ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የግንቦት 20 የድል በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ3 ሺህ 275 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ፡፡


የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍርዴ ቸሩ ዛሬ እንደገለጹት ታራሚዎች ይቅርታ የተደረገላቸው የክልሉ ይቅርታ ቦርድ ያቀረበውን መረጃ መሰረት በማድረግ ነው፡፡

በዚህም መሰረት በክልሉ ከሚገኙ ሁሉም ማረሚያ ቤቶች 78 ሴቶችን ጨምሮ 3 ሺህ 275 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጎላቸው ትላንት ተፈተው ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል።

በይቅርታ የተፈቱት ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ስነምግባር ያሳዩና በተግባርም ስለመታረማቸው የተረጋገጠላቸው ናቸው፡፡

ይቅርታው በሙስና፣ በአስገድዶ መድፈር፣ በሽብርተኝነት፣ ሀሰተኛ ገንዘብ በማባዛት፣ በመሰረተ ልማትና ሌሎች ከባድ ወንጀሎች ፍርድ የተሰጠባቸውን ታራሚዎች እንደማያካትትም ተናግረዋል።

በይቅርታ የተለቀቁ ታራሚዎችም ባጠፉት ጥፋት የተፀፀቱና የበደሉትን ህብረተሰብ በልማት ለመካስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ለታራሙና ለተፀፀቱ የህግ ታራሚዎች በዓመት ሁለት ጊዜ ይቅርታ እንደሚያደርግ ታውቋል።

ምንጭ፦ኢዜአ