ወጣቶች ከጥፋት እንዲቆጥቡ የአማራ ክልል መንግስት ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 5 ቀን ፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ወጣቶች እራሳቸውን ከጥፋት እንዲቆጥቡ የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬኝን ጉዳዮች ቢሮ ሃለፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በትናንትናው ዕለት በደብረ ማርቆስ በተከሰተው ግጭት 2 ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል እንደገቡ የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በማህበራዊ ድረ ገጻቸው እስፍረዋል።

በሶስት ሆቴሎች፣ ሁለት የፋይናንስ ተቋማት ፣ አንድ ቤትና አስር ተሽከርካሪዎች ላይም በግጭቱ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

በተለያዩ አካባቢዎች ተመሳሳይ ግጭቶች እንዲስፋፉ ለማድረግ ከፍተኛ ዘመቻ እየተደረገ መሆኑን የሚያሳዩ ተጨባጭ መረጃዎች
መገኘታቸውንም ነው አቶ ንጉሱ ያመላከቱት።

በዚህም ወጣቶች ተጨባጭነት በሌለው የሀሰት መረጃ በመነሳሰት አካባቢያቸውን የብጥብጥ ማዕከል ከማድረግ እንዲቆጠቡም ነው ጥሪያቸውን ያስተላለፉት።