በፓኪስታን በተፈጸመ ጥቃት 20 ሰዎች ሞቱ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 4 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን በተፈጸመ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት 20 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።

ጥቃቱ የተፈጸመው ፔሻዋር በተባለችው ግዛት አዋሚ ብሄራዊ ፓርቲ ባዘጋጀው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ነው ተብሏል።

በጥቃቱ ከሞቱት በተጨማሪም 69 ሰዎች ቆስለዋል የተባለው።

በተፈጸመው ጥቃት ከሞቱት ውስጥ በፓርቲው አካባቢውን ወክለው በምክር ቤት ይወዳደሩ የነበሩ ተሳታፊ ይገኙበታል ተብሏል።

በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የታሊባን ታጣቂ ቡድን ለጥቃቱ ሃላፊነቱን ወስዷል።


ምንጭ፦ አልጀዚራ