በሀዋሳ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች ማምሻውን ተከስቶ የነበረውን ግጭት የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀዋሳ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች ማምሻውን ተከስቶ የነበረውን ግጭት የማረጋጋት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

በሀዋሳ ከተማ አንዳንድ ቦታዎች ወጣቶች መንገዶችን በመዝጋትና ድንጋይ በመወርወር በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽ ጉዳዮች ቢሮ ሃለፊ አቶ ሰለሞን ሃይሉ ገልጸዋል።

 እንድ አቶ ሰለሞን ገለፃ አሁን ላይም በሃዋሳ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች የጸጥታ ሀይሎች ሁከቱን በማረጋጋት ላይ ናቸው።

 

በግጭቱ በሰዎችና ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፥ በሰውና ንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት እየተጣራና ነውም ብለዋል።

ወጣቱ የተለለያዩ ጥያቄዎች ሊኖሩት ቢችሉም ጥያቄዎቹ በህገመንግስት አግባብና በህግ መታየት የሚችሉበት አጋጣሚ እያለ ወደ ሁከትና ብጥብጡ በግባቱ ተገቢ ያለመሆኑን አስረድተዋል።

በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቱ የለያዩ መንስኤዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ የገለጹት ቢሮ ሃላፊው ከዚህ በጓላም መንግስት ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ እስኪያገኙ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ነው የገሉጹት።