ትራምፕ በቻይና ምርቶች ቀረጥ ጉዳይ ላይ እንደገና የመምከር ሀሳብ እንዳላቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ7፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትራምፕ በቻይና ምርቶች ቀረጥ ጉዳይ ላይ እንደገና የመምከር ሀሳብ እንዳላቸው ተገለጸ።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከከፍተኛ የንግድ አማካሪዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ሊመክሩ መሆኑን የትራምፕ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣናት ገልጸዋል ተብሏል።

 ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቻይና ምርቶች ላይ በጣሉት ቀረጥ ላይ ዋሽንግተን ማሻሻያ ካደረገች ቤጂንግ በአሜሪካ ምርቶች ላይ ለመጣል ያሰበችውን ቀረጥ የማንሳት ፍላጎት ያላት መሆኑን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገንግ ሹዋንግ ገልጸዋል።

አሁን ላይ ሀገራቱ በመካከላቸው ያለውን ወቅታዊ የንግድ ቅራኔ መፍታቱ ለሁቱም ሀገራት ጠቃሚ መሆኑን ነው ቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹዋንግ የተናገሩት።

በፕሬዚዳንት ትራምፕ ምክረ ሀሳብ በቻይና ምርቶች ላይ በተጣለው ቀረጥ ላይ ማሻሻያ ከተደረገ የቤጂንግን የአሜሪካ ምርቶችን የመግዛት ፍላጎት እንደሚያሳድገውና ለአሜሪካ ኢኮኖሚም ጠቃሚ መሆኑን ነው የተገለጸው።

ትራፕ ባሳለፍነው ማክሰኞ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ አሁን ላይ ከቻይና ጋር ያለው የንግድ ሁኔታ ያሳሰባቸውና በሚቀጥሉት ሳምንታት እልባት የሚሰጡ መሆናቸውን መግለፃቸውን ዘገባው አስታውሷል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ በትክክል ምን ርምጃ ሊወስዱ መሆኑን ያልገለጹት ትራምፕ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ዥ ጂንፕንግ ጋር ጥሩ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል ነው የተባለው።

ዋሽንግተን በዚህ የቀረጥ ጉዳይ ላይ ማስተካካያ የማታደርግ ከሆነ ቤጂንግ በበኩሏ ከአሜሪካ በምታስገባቸው አኩሪ አተር፣ ተሽከርካሪዎች፣ ኬሚካልና አውሮፕላኖች ላይ የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቷም ታውቋል።

ፕረዚዳንት ትራምፕ በቻይና ምርቶች ላይ ጥለውት የነበረው 50 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ቀረጥ ላይ ማሻሻያ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ባለፈው ጊዜ ቀረጡ ተጥሎባቸው የነበሩ የቻይና ምርቶች ላይ በአንደንዶቹ ላይ የሚነሳ፣ ቅናሽ የሚደርግና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ቀረጡ ከፍ ሊል እንደሚችል ተጠቁሟል።

ከትራንፕ አስተዳደር ሰዎች የወጡ መረጃዎች እንዳመላከቱትም በዚሁ ጉዳይ ላይ ረቂቅ ሰነድ የተዘጋጀ ሲሆን፥ በ1 ሺህ 300 የቻይና ምርቶች ላይ የቀረጥ ዝርዝር መውጣቱን ዘገባው የሚያመላክተው።

 

 

ምንጭ፦ reuters.com

የተተሮመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ