ሰሜን ኮሪያ እራሷን ከኒውኪሌር ነፃ እስካላደረገች የኢኮኖሚ ማዕቀቡ ቀጣይነት ይኖረዋል- አሜሪካ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ7፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰሜን ኮሪያ እራሷን ሙሉ በሙሉ ከኒውኪሌር ነፃ እስካላደረገች ድረስ የኢኮኖሚ ማዕቀቡ ቀጣይነት እንደሚኖረው የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ገልጸዋል።

ሰሜን ኮሪያ ከኒውኪሌር ፕሮግራም ሙሉ በሙሉ ነፃ መሆኗን ሳታረጋግጥ የኢኮኖሚ ማዕቀቡ እንደማይነሳላት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ከደቡብ ኮሪያና ጃፓን አቻቸው ጋር በሶውል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

 

በሲንገፓሩ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ውይይት ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የምታምደርገውን ወታደራዊ ልምምድ ልታቋርጥ የምትችል መሆኑን መግለፃቸው የቀጠናው ሀገራትን ትኩረት የሳበ በመሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠታቸው ነው የተገለጸው።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የምታደርገውን ወታደራዊ ልምምድ እንደምታቋርጥ የገለጹ ቢሆንም፥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ፖምፒዮ ሀገራቸው ከደቡብ ኮሪያና ጃፓን ጋር ያለው አጋርነት ተጠናክሮ እንቀጥል እየሰሩ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል።

የአሜሪካና የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ልምምድ ሰሜን ኮሪያ በስጋት የምታየው ቢሆንም፥ ለጃፓንና ደቡብ ኮሪያ ደህንነት ጠቀሚ መሆኑን ዘገባው ያስረዳል።

ሰሜን ኮሪያ የአካቢው ልሳነ ምድር ከኒውኪሌር ፕሮግራም ለማጽዳት ቀደም ሲል የገባችው ቃል የሚበረታታ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ በምን መንገድ ይህንን ስምምነተ ተገባረዊ ለማድረግና የኒውኪሌር የጦር መሳሪያ መጠቀሟን ለማቆም እንደምትችል ግን ግልጽ አይደለም ብለዋል።

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የሲንጋፖር ግንኙነት ለሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት መሰረት የሚጥል ቢሆንም የሰሜን ኮሪያ መገናኛ ብዙሃን በኒውኪሌር ፕሮግራም ዙሪያ ፒያንግ ያንግ በሂደት ለውጥ ማድረግ በምትችልበት ሁኔታ ላይ ዋሽንግተን መስማማቷን መግለፃቸው መሰረት የሌለው ሀሳብ መሆኑን ነው ሚስተር ፖምፒዮ የገለጹት።

የዋሽንግተን አቋም ፒያንግ ያንግን ሙሉ በሙሉ ከኒውኪሌር ፕሮግራም ነፃ ማድረግና በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ኋላ እንዳትመለስ ማድረግ ነው ተብሏል።

ሁለቱ ፕሬዚዳንቶች በሲንጋፖር ተገናኝተው በምን ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ እንደደረሱ ሚስተር ፖምፒዮ በዝርዝር ያለማስረዳታቸውንም ነው ዘገባው የሚያመላክተው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፖምፒዮ መግለጫውን የሰጡት የሁለቱ ሀጋራት መሪዎች በሲንጋፖር ከተገናኙ ከቀናት በኋላ መሆኑን ዘገባው አስታውሷል።

 

ምንጭ፦bbc.com

የተተረጎመውና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ