በዚህ ክረምት ከ4 ቢሊየን በላይ ችግኞች ለመትከል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው - የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር

አዲስ አባባ፣ ግንቦት 07፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዚህ ክረምት ከ 4 ነጥብ ሶስት ቢሊየን በላይ ችግኞችን ለመተከል ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ ከአንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት በላይ ለማልማት የታቀደ ሲሆን ፥ አሁን ላይ ከ 300 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መዘጋጀቱም ነው የተገለጸው።

ለዚህ ፕሮግራም ከአንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን በላይ ችግኞች መዘጋጀታቸውንም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የደን ልማት ጄነራል ዳይሬክተር አቶ ቢተዉ ሽባባዉ ገልጸዋል።

አሁን ላይ ያለዉን ሀገራዊ የደን ሽፋን ለማጥናት የሚያስችል ጥናት ለማካሄድ ዝገጀት እየተደረገ ሲሆን፥ ጥናቱ ያለዉን የደን ሽፋን ለማወቅ የሚያስቸልና ለቀጣይ የልማት እቅድ ስራዎች ግብዓት በመሆን የሚያገለግል መሆኑን ነው አቶ ቢተው የገለጹት።

የችግኝ ተከላው በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚጀመርም ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት።

ሀገሪቱ በሚቀጥሉት ሁለት አመታት ማብቂያ ላይ አጠቃላይ የደን ሽፏኗን ወደ 20 በመቶ ከፍ ለማድረግ እቅድ ይዛ እየሰራች መሆኑም ነው የተገገለጸው።


በኃሀይለሚካኤል አበበ