የሳዑዲ ጥምር ኃይል የየመን ወደብን አጠቃ

አዲስአበባ፣ ሰኔ 6፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው ጥምር ኃይል በየመን የሚገኘውን የሁዳይዳ ወደብን ማጥቃጡ ተገለጸ፡፡

ጥምር ኃይሉ ጥቃቱን ሊሰነዝር የቻለው አካባቢውን እንዲለቅ የተቀመጠለትን ቀነ ገደብ በመተላለፉ ነው ተብሏል፡፡

መጀመሪያ የሁቲይ ታጣቂ ኃይሎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ሰላማዊ የሆነ ዲፕሎማሳዊ ጥረት ማካሂዱን ጥምር ኃይል አስታውቋል፡፡

ኃላም ይህ ባለመሳካቱ ጥምር ኃይሉ የታጣቂዎቹን የጦር ሰፈር በምድርና በአየር ኃይል በመታገዝ አካባቢውን መደብደቡን ነው የተገለጸው፡፡

ሁዳይዳ ወደብ የሰብዓዊ እርዳታ የሚገባበት ዋነኛ የመተላለፊያ በር ነው ተብሏል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በየመን ሰባት ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች የዕለት እርዳታ የሚፈልጉ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

በየመን በሚደረገው የእርስ በርስ ጦርነት እስከአሁን ድረስ የ10 ሰዎች ህይወት መቀጠፉንና ትልቁ የሰብዓዊ ቀውስ መሆኑንም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡

 


ምንጭ፦ቢቢሲ
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ