የኮሪያ ልሳነ ምድርን ከኑክሌር ነፃ ለማድረግ ኪም ጆንግ ኡን ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ ፣5፣2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኪም ጆንግ ኡን የኮረያን ልሳነ ምድርን ከኑክሌር ነፃ ለማድረግ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ስምምነት ላይ ደረሱ።

መሪዎቹ ታሪካዊ ነው በተባለው በዛሬው የሲንጋፓር ግንኙነታቸው በተለያዩ ጉዳዮች የመግባቢያ ስምምነት እንደተፈራረሙ ታውቋል።

የመሪዎቹ ስምምነት የኮሪያ ሰላጤን ብሎ የአለምን ደህነት ለማረጋገጥ እንዲሁም አካባቢውን ከኑክሌር ጦር መሳሪያ ነፃ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል። 

የሀገራቱን ግንኙነት ማሻሸሻል እና የኮሪያ ቀጠናን ሰላም ማረጋገጥ የስምምነቱ አንድ አካል መሆኑ ተገልጿል።

የሰሜን ኮሪያ እና አሜሪካ ዜጎችን ሰላም እና ብልፅግና ፍላጎት ለመመለስ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል መወሰናቸው ተነግሯል።

ሌላው የስምምነት ነጥብ በቬትናም ጦርነት ምክንያት የጦር እስረኛ የሆኑ አሜሪካውያን ወደ ሀገራቸው መመለስ እንዲችሉ ተስማምተዋል።

በሀገራቱ መካከል በመሪዎች ደረጃ ይፋዊ የሆነ ስምምነት ሲደረስ የመጀመሪው ሲሆን፥ ለበርካታ አስርተ ዓመታት እርስ በእርሳቸው በጥላቻ እንጂ በበጎ ሳይተያዩ የቆዩትን ሁለቱ ሀገራት ወደ ፊት ለማቀራረብ ተስፋን የፈነጠቀ መሆኑ ተገልጿል።

መሪዎቹ በዛሬው ዕለት የደረሱባቸውን ስምምነቶች በቁርጠኝነት እና በፍጥነት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸው አስታውቀዋል።

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች መገናኘት እውን ይሆነው የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፒዮ እና የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ባደረጉት ተከታታይ ውይይት መሆኑ ይታወሳል።

ምንጭ፥ አልጄዚራ