የፊሊስጤሙ መሪ መሃሙድ አባስ ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የፊሊስጤሙ መሪ መሃሙድ አባስ ባለፈው ሳምንት የተደረገላቸውን ቀላል የቀዶ ህክምና ተከትሎ በተፈጠረ ችግር ሆስፒታል መግባታቸው ተነገረ።

የፊሊስጤም ባለስልጣናት እንዳስታወቁት፥ መሃሙድ አባስ በዛሬው እለት ነው ዌስት ባንክ የሚደኝ ሆፒታል ለህክምና የገቡት።

የ82 ዓመቱ መሃሙድ አባስ ወደ ለህክምና ሆስፒታል ሲገቡም በአንድ ሳምንት ወስጥ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑም ተነግሯል።

አባስ ባሳለፍነው ሳምንት ማክሰኞ ጆሯቸው ላይ ቀላል ቀዶ ህክምና አድርገው የነበረ ሲሆን፥ በዚህ ጋር ተያይዞ በመጣ ችግር ነው ሆስፒታል የገቡት።

የፊሊስጤም ባለስልጣናት እንደተናገሩት መሃሙድ አባስ በዛሬው እለት ተመልሰው ወደ ሆስፒታል የገቡት የቀዶ ህክምናውን ተከትሎ የሰውነታቸው ሙቀት በከፍተኛ መጠን በመጨመሩ ነው።

በአሁኑ ወቅትም አባስ በመልካም ጤንነት ላይ አንደሚገኙ የኢስቲሻሪ ሆስፒታል ሚዲካል ማናጀር ዶክተር ሰኢድ ሳራህነ መግለፃቸውን የፊሊስጤዉ የዜና ድርጅት ዋፋ ዘግቧል።

ምንጭ፦ www.reuters.com