በሆለታ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 38 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሆለታ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ንብረት ማውደሙን የከተማዋ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

እንደ ጽህፈት ቤቱ ገለጻ በእሳት አደጋው በሆለታ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበረ 38 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

የእሳት አደጋውንም በአካባቢው ነዋሪ፣ ፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲሁም ከአዲስ አበባ በተገኘ የእሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች ድጋፍ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።

የእሳት አደጋው መንስኤ ለጊዜው እስካሁን ያልታወቀ መሆኑን ያስታወቀው ጽህፈት ቤቱ፥ መንስኤው እየተጣራ መሆኑን ገልጿል።