ፊሊፒንስ ዜጎቿ ወደ ኩዌት እንዳይገቡ የጣለችውን እገዳ አነሳች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት09 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፊልፒንስ ወደ ኩዌት ሄደው ሰራተኞች እንዳይቀጠሩ ጥላው የነበረውን እገዳ ከሳለፍነው ሮብ የሁለቱ ሀጋራት ዲፕሎሚያሲያው ውይይት በኋላ ማንሳቷን ገለጸች።

የፌሊፒንስ ሰራተኞች ወደ ኩዌት ሄደው እንዳይቀጠሩ ተጥሎ የነበረው እገዳ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ የፊልፒንስ ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ሮዋ ዱተርቴ ማዘዛቸው ተገልጿል።

 ሁለቱ ሀገራት በሰራተኞች አያያዝ ላይ የሁለትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ ከተፈራረሙና የኮዌት ልዩ መልክተኛ አብደላህ ማማኦ ወደ ፊሊፒንስ ካቀኑ በኋላ ፕሬዚዳንቱ እገዳውን ያነሱ መሆኑ ነው የተገለጸው።

የኩዌት ልዩ መልክተኛ አብደላህ ማማኦ ሀገራቸው በሰራተኛ እና አሰሪነት ጉዳዮች ላይ ከፊሊፒንስ ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ሰነድ በማክበር የሰራተኞች መብትና ደህንነት ለማስከበር በቁርጠኝነት እንደምትስራ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጸቸው ታውቋል።

ባሳለፍነው የፈረንጆቹ የካቲት ወር በኩዌት የፊሊፒንስ የቤት ሰራተኞች ህይወት መጥፋትን ተከትሎ በሁለቱ አገራት መካከል በተፈጠረው ውጥረት የፊሊፒንስ መንግስት ሰራተኞቹ ወደ ኮዌት እንዳይገቡ ገደብ ጥሎ የነበረ መሆኑ ይታውሳል።

አሁን ላይ ሁለቱ ሀገራት የተፈራረሙት የሁለትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት የቤት ሰራተኞችና በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ የፊሊፒንስ ዜጎች በኮዌት ለመቀጠር የሚያስችል እንደሆነ ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።

አሁንም 260 ሺህ ያህል የፊሊፒንስ ዜጎች ኩዌት ውስጥ በስራ ላይ ያሉ ሲሆን፥ ከነዚህም መካከል ግማሽ ያህሉ የቤት ሰራተኞች መሆነቸውም ነው የተገለጸው።

 

 

 

 

 

ምንጭ፦ aa.com.tr

 

የተተረጎመና የተጫነው፦ በእንቻለው ታደሰ