ናይጄሪያ በ7 ቢሊየን ዶላር የባቡር መስመር ልትዘረጋ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ)ናይጄሪያ በ6 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የባቡር መስመር እንዲዘረጋላት ለቻይናው ሲቪል ኢንጂነሪንግ የኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ድርጅት መስጠቷን አስታወቀች፡፡

የባቡር መስመሩ የንግድ ማዕከል ከሆነችው ሌጎስ ጋር በደቡብ ምዕራብ በኩልና በሰሜን ደግሞ ከካኖ ጋር ለማገናኘት ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የናይጄሪያ የትራንስፖርት ሚኒስትር ግንባታው ከሁለት እስከ ሦስት ዓመታት ሊወስድ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

ይህ የቻይና ድርጅት ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ የሌጎስ-ካኖ የባቡር ፕሮጀክት ግንባታ ላይ እንደተሳተፈ ተገልጿል፡፡

የባቡር መስመሩ ምን ያህል ኪሎሜትሮችን እንደሚሸፍን የተገለጸ ነገር የለም፡፡

ምንጭ፦ሲጂቲኤን
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ