ተመድ የአሚሶምን የቆይታ ጊዜ በሁለት ወራት አራዘመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮን (አሚሶም) የቆይታ ጊዜ በሁለት ወራት እንዲራዘም የውሳኔ ሐሳብ አሳለፈ፡፡

የውሳኔ ሐሳቡን እስከ ሀምሌ መጨረሻ ያዛወሩት ያለምንም ተቋውሞ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ እስከ ጥቅምት 10 ድረስ በሶማሊያ ያለውን ኃይል ከ22 ሺህ 126 ወደ 20 ሺህ 626 እንዲቀንስም ጥሪ አቅርቧል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ተመድ የቄሳቁስ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስቧል፡፡

በሶማሊያ የተመድ ዋና ጸሐፊ ተወካይ ማይክል ኬይቲንግ አሚሶም የማይተካ ሚና ለሀገሪቷ እየሰጠ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

10 ሺህ 900 የሚደርሱ የሶማሊያ የጦር ኃይል አባላት ከአሚሶም ጋር በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

የአፍሪካ ህብረት እና የተመድ ዋና ጸሐፊ ልዑክ የተሳካ የፀጥታ ሽግግር በሀገሪቷ እንዲኖር በመስራት ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡

የሀገሪቷን የሽግግር መንግስት ለመደገፍ ወደ ሶማሊያ የገባው አሚሶም ተልዕኮውን በ2020 ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

 


ምንጭ፦ሲጂቲኤን
በአብርሃም ፈቀደ ወደ አማርኛ ተመለሰ