ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይትኛ ሙዚቃ ዘፋኙ ኮይሻ ሴታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ድምጻዊ ኮይሻ ባጋጠመው የጤና እክል ሳቢያ ለህልፈት መዳረጉን ለማወቅ ተችሏል።

ድምጻዊው የወላይትኛ ሙዚቃን ለአድማጮች በማድረስ ቀዳሚው እንደነበር ይነገራል።

በ1984 ዓ.ም በኢትዮ ሙዚቃ ቤት አማካይነት ለሕዝብ ባደረሰው የሙዚቃ ካሴት የወላይታን ሕዝብ ሙዚቃና ባሕል አስተዋውቋል።

ድምጻዊ ኮይሻ ሴታ በባህል ሙዚቃው ዘርፍ ድንቅ አበርክቶ ነበረው።

ኮይሻ ሴታ አዲስ የሙዚቃ ካሴት ስራውን ለአድማጮች ለማድረስ እየሞከረ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

የኮይሻ ሴታ አስከሬን ቀብሩ ወደ ሚፈጸምበት ደቡብ ክልል ወላይታ ሶዶ እንዲሸኝ ተደርጓል።

ወላሎ አያና እና አሌ ጀናው ሙዚቃዎቹ በሙዚቃ አድማጮች ዘንድ በስፋት ይታወሳሉ።

ተጨማሪ መረጃ ከኢዜአ