የረመዳን ጾም ጨረቃ ከታየች ከነገ በስቲያ ጨረቃ ካልታየች ደግሞ ሃሙስ ይገባል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 439ኛው የረመዳን ጾም ጨረቃ ከታየች ከነገ በስቲያ ረቡዕ ጨረቃ ካልታየች ደግሞ ሃሙስ እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።

የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ሼህ መሃመድ አሚን ጀማል ዑመር፥ ታላቁና በናፍቆት የሚጠበቀው የረመዳን ጾም ቀን በጸሎት ሌሊት ደግሞ በኢባዳ ነብስ የሚጸዳበት ነው ብለዋል።

ሙስሊሙ ማህበረሰብም ይህን ቅዱስ እና ታላቅ የጾም ወቅት፥ ሰደቃ በማብዛት፣ የታመሙትን በመጠየቅና ከተቸገረው ጎን በመሆን ሀይማኖታዊ ግዴታውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

የጾም ወቅቱ ከሚፈቅዳቸው በጎ ምግባራት ጎን ለጎንም ሙስሊሙ ማህበረሰብ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ፕሬዚዳንቱ ጠይቀዋል።


በትዕግሰት አብርሃም