የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

አዲስ አባባ፣ ግንቦት 6፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም ባንክ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ማክሃተር ዲዮፕ የሦስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ከሦስት ቀናት በኃላ ኢትዮጵያ ይገባሉ፡፡

ጉብኝቱ የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱ በቆይታቸው ከፌዴሪ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ይወያያሉ፡፡

እንዲሁም ከገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም ተከስተ ጋርም ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ከዓለም አቀፍ ተቋማት መካከል ከተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ ኮሚሽንና ከአፍሪካ ህብረት ጋር ቆይታ ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡