የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከኳታሩ ኤሚር ጋር ተወያዩ

አዲስ አባባ፣ ግንቦት 6፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከኳታሩ ኤሚር ሼክ ተሚም ቢን ሃማድ አል ተሃኒ ጋር በዶሃ ተወያዩ፡፡

ዶክተር ወርቅነህ ከኢፌዴሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላከ ደብዳቤም ለኳታሩ ኤሚር አስረክበዋል፡፡

ደብዳቤው የሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማስቀጠልና ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡

ባለፈው ዓመት የኳታሩ ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን አህመድ አልታኒ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

በዚህም የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚና የኢንቨስትመንት እንዲሁም ፖለቲካዊ ግንኙነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መምከራቸው አይዘነጋም።