የጤፍ የአዕምሮዊ ንብረት ባለቤትነት መብትን ለማስመለስ ጥረት እየተደረገ ነው

አዲስ አባባ፣ ግንቦት 6፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤፍ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት መብትን ኢ-ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ከወሰደው የሆላንድ ኩባንያ ለማስመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ እያደረገ ካለው ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች ጎን ለጎን የፍርድ ሂደት ለመጀመር ለጠቅላይ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ሰነዶች ማስረከቡን ገልጿል፡፡

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የሚመራው ብሔራዊ ኮሚቴ ለበርካታ ወራት ሲሰራ የቆየውን የዝግጅት ስራ ማጠናቀቁንም አስታውቋል።

ይህን ተከትሎ የፍርድ ሂደቱ እንዲጀመር ሰነዶችን ለጠቅላይ አቃቤ ህግ ማስተላለፉንም ነው ያስታወቀው፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጤፍ የባለቤትነት መብት ለኢትዮጵያ እስከሚመለስ ድረስ ጠንክሮ እንደሚሰራም ገልጿል።