ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ የህግ ድግሪ የላቸውም ያለቻቸውን 256 ዳኞች ከስራ አሰናበተች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) የዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ የህግ ድግሪ የሌላቸውና በሙስና የተጠረጠሩ ያሏቸውን 256 ዳኞች ከስራ ማሰናበታቸው ተነገረ።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዳኞቹ ተግባርና ሀላፊነታቸውን በሚጠበቅባቸው ደረጃ ባለወጣታቸው ከስራ እንዳሰናበቷቸው ነው የተነገረው።

 ከ256 ዳኞቹ መካከል ላልተወሰነ ጊዜ ከስራ የታገዱ፣ ሙሉ በሙለ የተሰናበቱ፣ በጥሮታ እና እራሳቸውን ከሀላፊነት ያነሱ እንደሚገኙበት ታውቋል።

 የሀገሪቱ ፍትህ ሚኒስትር ምዋባ አሌክሲስ የህግ ስራ የገንዘብ ምንጭ ተደርጎ መውሰድ እንደማያስፈልግ ገልፀው የህግ ዲግሪ ሳይኖራቸው ወደ ስራ የተሰማሩትን በድፍረት የተሞላ ተግባር ሲሉ ተናግረዋል።

 

ከዚህ በፊት በፈረንጆቹ 2009 ከሙስና ክስ ጋር በተያያዘ ሀገሪቱ 96 ዳኞችን ከስራ አሰናብታ ነበር ተብሏል።

ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት 4 ሺህ የሚጠጉ ዳኞች እንዳሏት ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት።

ምንጭ፦ አልጂዚራ