በሶሪያ የተፈፀመውን የኬሚካል ጥቃት የሚያጣራ ቡድን ፈቃድ ተሰጠው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) በሶሪያ የተፈፀመውን የኬሚካል ጥቃት የሚያጣሩ ባለሙያዎች ምርመራ እንዲያደርጉ ተፈቀደላቸው።

ይህ የኬሚካል መሳሪያ አጣሪ ቡድን ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ወደ ስፍራው ቢያመሩም ምርመራ እንዲያደርጉ ሳይፈቀድላቸው እንደቆዩ ታውቋል።

አጣሪ ቡድኑ ወደ አካባቢው በማምራትም የኬሚካል ጥቃቱ መፈፀም አለመፈፀሙን ማረጋገጥ የሚያስችሉ የአፈርና ሌሎች ናሙናዎችን እንደሚሰበስብ ይጠበቃል።

ሆኖም የኬሚካል ጥቃት በተፈፀመበት ስፍራ ሩሲያ የምትንቀሳቀስ በመሆኑ ናሙናዎችን በማጥፋት የምርመራውን ውጤት ልታዘባ ትችላች የሚል ስጋት እየተነሳ ይገኛል።

ሩሲያ በበኩሏ በአካባቢው የምርመራውን ውጤት ሊያዛባ የሚችል ምክንያት እንዳማይኖር በመናገር ላይ ትገኛለች።

እንዲሁም ይህ የምዕራባውያኑ ክስ ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኘና በመረጃ ያልተረጋገጠ እንደሆነ ሩሲያ ትገልፃለች።

ሶሪያና ሩሲያ ይህ የተከለከለ የጦር መሳሪያ ጥቃት እንዳልተፈፀመ በመግለፅ ምዕራባውያኑ የሚቀርብባቸውን ክስ ውድቅ ያደርጋሉ።

ከአሜሪካና አጋሮቿ ጥቃት በኋላ በሶሪያ መንግስት ይዞታዎች ላይ የሚሳኤል ጥቃት እንደተፈፀመና ሀላፊነቱን የወሰደ አካል እንደሌለ ተነግሯል።

አሜሪካም በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ምንም አይነት ወታደራዊ እንቅስቀሴ እያደረገች አለመሆኑን አስታወቃለች።

በኬሚካል ጥቃቱ የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ አሜሪካና አጋሮቿ በሶሪያ መንግስት ይዞታ ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ