አሜሪካና አጋሮቿ በሶሪያ ላይ የዓየር ጥቃት ፈፀሙ

አዲስ አበባ ሚያዝያ 6፣ 2010(ኤፍ.ቢ.ሲ) ዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ በሶሪያ በተመረጡ በመንግስት ይዞታዎች ላይ የቦምብ ጥቃት ፈፀሙ።

ጥቃቱ ባለፈው ሳምንት በሶሪያ ዱማ ለተፈፀመው የኬሚካል ጥቃት ምላሽ መሆኑ ተመልክቷል።

ፍንዳታዎች የሀገሪቱ መዲና ደማሰቆን እና ሀምስ አቅራቢያን ማናወጣቸው ነው የተነገረው።

ማምሻውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባስተላለፉት ፥ ሀገራቸው አሜሪካ፣ ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ በሶሪያ የኬሚካል ጦር መሳሪያ ምርትን እና ስርጭትን ለማሰቆም ድብደባ መካሄዱን ይፋ አድርገዋል።

ፔንታጎንም ባወጣው መግለጫ ድብደባው በደማሰቆ የባዮሎጂካል እና ኬሚካል መሳሪያ ለማምረት እና ለምርምር የሚያገለግል ማዕከል፣ በሆምስ የሚገኝ የኬሚካል መሳሪያ ማከማቻ ስፍራ እና ማዘዣ ኢላማ መደረጋቸውን ነው ያስታወቀው።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ