የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ልባሽ ጨርቆች ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ እያገዱ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ)የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ልባሽ ጨርቆች ወደ አገሮቻቸው እንዳይገቡ እገዳ መጣል ጀምረዋል።

በተለይም ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳ ከአሜሪካና እንግሊዝ በሚገቡ ልባሾች ጨርቆች ላይ ትኩረት በማድረግ እገዳ ጥለዋል።

ሀገራቱ የእገዳ እርምጃውን ለመውሰድ የተገደዱት ከአሜሪካ እና አውሮፓ የሚገቡ ልባሽ ጨርቆች እና ከቻይና በቅናሽ ዋጋ የሚገቡ አልባሳት በሀገር ውስጥ ፋብሪካዎቻቸው ላይ ስጋት በመደቀናቸው ነው።

ሀገራቱ እርምጃው የንግድ ስምምነትነ የሚጥስ ነው ከምትለው አሜሪካ የማእቀብ ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ይግኛል።

ሆኖም የጣሉት እገዳ የሀገር ውስጥ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎችን በማነቃቃት የወጪ ንግዳቸውን ይደግፋል ብለው ተስፋ አድርገዋል።

 

ምንጭ፦አልጀዚራ
ተተርጉሞ የተጫነው፦ በአብረሃም ፈቀደ