ኦክስፋም በሀይቲ ሰራተኞቹ ለፈጠሩት የወሲብ ቅሌት ይቅርታ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2010 (ኤፍ. ቢ. ሲ ) በሐይቲ በ2010 በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የደረሰውን የሰብዓዊ ቀውስ ተከትሎ ለዕርዳታ የገቡት የኦክስፋም ሰራተኞች ከወሲብ ቅሌት ጋር ተያያዘ ክስ ሲቀርብባቸው ቆይቷል። ይህንንም ተከትሎ ኢክስፋም በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።

ጉዳቱ የከፋውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በሀገሪቱ ለረድኤት ስራ የተመደቡ የኦክስፋም ሰራተኞች ለወሲብ ክፍያ ሲፈፅሙ እንደነበር የተረጋገጠው በዚህ ወር መጀመሪያ ነበር።

የኦክስፋም ክልላዊ ዳይሬክተር ሲሞን ታይስሃርስት በሃይቲ የፕላንና የውጭ ትብብር ሚኒስትር አቭዮል ፍሌውራንት ጋር በ2011 ላይ ስለተፈጠረው ክስተት ተገናኝተው መነጋገራቸውን ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም የሃይቲ መንግስት ለሚያደርገው ተጨማሪ ማጣራት ተቋማቸው እንደሚተባበር ነው ያረጋገጡት።

ይህንን ተከትሎ ኦክስፋም ባካሄደው የውስጥ ምርመራ ሰባት ሰራተኞቹ ድርጅቱን መልቀቃቸውን አስታውቋል።

አራት ሰራተኞች በቀጥታ ሲባረሩ የሐይቲ ይሬክተር በመሆን ያገለገሉት ሮናልድ ቫንሁዋን ዌርሚን ጨምሮ ሦስት ግለሰቦች በፍቃደኝነት ስራ መልቀቃቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም ምስክሮች እየተመረመሩ ከነበሩ የኦክስፋም ሰራተኞች ዛቻ እንደደረሰባቨው ነው ያመለከቱት።

የተፈጸመው ድርጊት የድርጅቱን ክብርና በእርዳታ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን ሊጎዳ እንደሚችል ተነግሯል።

የኦክስፋም ስራ አስፈጻሚው ማርክ ጎልድሪንግሃም ባለፈው ሳምንት በእንግሊዝ ፓርላማ አባላት ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡

ስራ አሰውፈጻሚው ኦክስፋም ባደረሰው ጉዳት የሐይቲን መንግስት ይቅርታ ጠይቀዋል።

በተያያዘም የወሲብ ቅሌት ጉዳይ ከተሰማ በኋላ ወደ 26 የሚጠጉ አዳዲስ አስተዳደራዊ ጥሰቶችን ለድርጅቱ መቅረባቸው ተነግሯል።

 

ምንጭ፦ አልጀዚራ

ተተርጉሞ የተጫነው፦ በአብረሃም ፈቀደ