የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያን ሊገበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው።

ፕሬዚዳንት ኦቢያንግ ኒጎሚያ ባሶንጎ ለሶስት ቀናት ያክል በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በፕሬዚዳንቱ የሚመራው የልዑካን ቡድን ነገ አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሬዚዳንት ኦቢያንግ ኒጎሚያ በቆይታቸው ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ እና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሏል።

በተያያዘ ዜና የሁለቱ አገራት የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ረቡዕ ይካሄዳል።

በስብሰባው የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና የኢኳቶሪያል ጊኒ የውጭ ጉዳይና ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ስሞን ኦዮኖ ኢሶኖ አንጉዌ ይገኛሉ።

በጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባው ላይም የሁለቱ አገራት ግንኙነት በሚጠናከሩባቸው ጉዳዮች ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሁለቱ አገሮች ይፋ የሆነ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1970ዎቹ ነው።